1 Chronicles (Amharic)
1
1:1b.1CH.001.001አዳም፥ ሴት፥ ሄኖስ፥ ቃይናን፥ መላልኤል፥
1:3b.1CH.001.003ያሬድ፥ ሄኖክ፥ ማቱሳላ፥ ላሜሕ፥
1:4b.1CH.001.004ኖኅ፥ ሴም፥ ካም፥ ያፌት።
1:5b.1CH.001.005የያፌት ልጆች፤ ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥
1:6b.1CH.001.006ያዋን፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ።
1:7b.1CH.001.007የጋሜርም ልጆች፤ አስከናዝ፥ ሪፋት፥ ቴርጋማ። የያዋንም ልጆች፤ ኤሊሳ፥ ተርሴስ፥ ኪቲም፥ ሮድኢ።
1:8b.1CH.001.008የካምም ልጆች፤ ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን።
1:9b.1CH.001.009የኩሽም ልጆች፤ ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰብቃታ። የራዕማም ልጆች፤ ሳባ፥ ድዳን።
1:10b.1CH.001.010ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ኃያል መሆንን ጀመረ።
1:11b.1CH.001.011ምጽራይምም ሉዲምን፥ ዐናሚምን፥ ላህቢምን፥
1:12b.1CH.001.012ነፍተሂምን፥ ፈትሩሲምን፥ ፍልስጥኤማውያን የወጡበትን ከስሉሂምን፥ ከፍቶሪምን ወለደ።
1:13b.1CH.001.013ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥
1:14b.1CH.001.014ኬጢን፥ ኢያቡሳዊውን፥ አሞራዊውን፥
1:15b.1CH.001.015ጌርጌሳዊውን፥ ኤዊያዊውን፥ ዐርካዊውን፥
1:16b.1CH.001.016ሲኒያዊውን፥ አራዴዎንን፥ ሰማሪዎንን፥ አማቲን ወለደ።
1:17b.1CH.001.017የሴምም ልጆች፤ ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ዑፅ፥ ሁል፥ ጌቴር፥ ሞሳሕ።
1:18b.1CH.001.018አርፋክስድም ቃይንምን ወለደ፤ ቃይንምም ሳላን ወለደ፤ ሳላም ዔቦርን ወለደ።
1:19b.1CH.001.019ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ በዘመኑ ምድር ተከፍላለችና የአንደኛው ስም ፋሌቅ ተባለ፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነበረ።
1:20b.1CH.001.020ዮቅጣንም አልሞዳድን፥
1:21b.1CH.001.021ሣሌፍን፥ ሐስረሞትን፥ ያራሕን፥ ሀዶራምን፥
1:22b.1CH.001.022አውዛልን፥ ደቅላን፥ ዖባልን፥ አቢማኤልን፥
1:23b.1CH.001.023ሳባን፥ ኦፊርን፥ ኤውላጥን፥ ዮባብን ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ነበሩ።
1:24b.1CH.001.024ሴም፥ አርፋክስድ፥ ሳላ፥ ዔቦር፥ ፋሌቅ፥
1:26b.1CH.001.026ራግው፥ ሴሮሕ፥ ናኮር፥ ታራ፥ አብርሃም የተባለ አብራም።
1:28b.1CH.001.028የአብርሃምም ልጆች፤ ይስሐቅ፥ እስማኤል።
1:29b.1CH.001.029ትውልዳቸውም እንደዚህ ነው። የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፤ ከዚህ በኋላ ቄዳር፥ ነብዳኤል፥ መብሳም፥
1:30b.1CH.001.030ማስማዕ፥ ዱማ፥ ማሣ፥ ኩዳን፥ ቴማን፥
1:31b.1CH.001.031ኢጡር፥ ናፌስ፥ ቄድማ፤ እነዚህ የእስማኤል ልጆች ናቸው።
1:32b.1CH.001.032የአብርሃምም ገረድ የኬጡራ ልጆች፤ ዘምራን፥ ዮቅሳን፥ ሜዳን፥ ምድያም፥ የስቦቅ፥ ስዌሕ። የዮቅሳንም ልጆች፤ ሳባ፥ ድዳን።
1:33b.1CH.001.033የምድያምም ልጆች፤ ጌፌር፥ ዔፌር፥ ሄኖኅ፥ አቢዳዕ፥ ኤልዳዓ። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ነበሩ።
1:34b.1CH.001.034አብርሃምም ይስሐቅን ወለደ። የይስሐቅም ልጆች ዔሳውና እስራኤል ነበሩ።
1:35b.1CH.001.035የዔሳው ልጆች፤ ኤልፋዝ፥ ራጉኤል፥ የዑስ፥ የዕላም፥ ቆሬ።
1:36b.1CH.001.036የኤልፋዝ ልጆች፤ ቴማን፥ ኦማር፥ ስፎ፥ ጎቶም፥ ቄኔዝ፥ ቲምናዕ፥ አማሌቅ።
1:37b.1CH.001.037የራጉኤል ልጆች፤ ናሖት፥ ዛራ፥ ሣማ፥ ሚዛህ።
1:38b.1CH.001.038የሴይርም ልጆች፤ ሎጣን፥ ሦባል፥ ጽብዖን፥ ዓና፥ ዲሶን፥ ኤጽር፥ ዲሳን።
1:39b.1CH.001.039የሎጣንም ልጆች፤ ሖሪ፥ ሔማም፤ ቲሞናዕ የሎጣን እኅት ነበረች።
1:40b.1CH.001.040የሦባል ልጆች፤ ዓልዋን፥ ማኔሐት፥ ዔባል፥ ስፎ፥ አውናም። የጽብዖንም ልጆች፤ አያ፥ ዓና።
1:41b.1CH.001.041የዓና ልጅ፤ ዲሶን። የዲሶንም ልጆች፤ ሔምዳን፥ ኤስባን፥ ይትራን፥ ክራን።
1:42b.1CH.001.042የኤጽር ልጆች፤ ቢልሐን፥ ዛዕዋን፥ ዓቃን። የዲሳን ልጆች፤ ዑፅ፥ አራን።
1:43b.1CH.001.043በእስራኤልም ልጆች ላይ ገና ንጉሥ ሳይነግሥ በኤዶምያስ ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው። የቢዖር ልጅ ባላቅ፤ የከተማይቱም ስም ዲንሃባ ነበረ።
1:44b.1CH.001.044ባላቅም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የባሶራ ሰው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ።
1:45b.1CH.001.045ኢዮባብም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የቴማን አገር ሰው ሑሳም ነገሠ።
1:46b.1CH.001.046ሑሳምም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ በሞዓብ ሜዳ ምድያምን የመታው የባዳድ ልጅ ሃዳድ ነገሠ፤ የከተማይቱም ስም ዓዊት ነበረ።
1:47b.1CH.001.047ሃዳድም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የመሥሬቃ ሰው ሠምላ ነገሠ።
1:48b.1CH.001.048ሠምላም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ በወንዙ አጠገብ ያለችው የረሆቦት ሰው ሳኡል ነገሠ።
1:49b.1CH.001.049ሳኡልም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ነገሠ።
1:50b.1CH.001.050በኣልሐናንም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ ሃዳድ ነገሠ፤ የከተማይቱም ስም ፋዑ ነበረ፤ ሚስቱም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ መሄጣብኤል ነበረች፤ ሃዳድም ሞተ።
1:51b.1CH.001.051የኤዶምያስም አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ቲምናዕ አለቃ፥ ዓልዋ አለቃ፥ የቴት አለቃ፥
1:52b.1CH.001.052አህሊባማ አለቃ፥ ኤላ አለቃ፥ ፊኖን አለቃ፥
1:53b.1CH.001.053ቄኔዝ አለቃ፥ ቴማን አለቃ፥ ሚብሳር አለቃ፥
1:54b.1CH.001.054መግዲኤል አለቃ፥ ዒራም አለቃ፤ እነዚህ የኤዶምያስ አለቆች ነበሩ።
2
2:1b.1CH.002.001የእስራኤልም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥
2:2b.1CH.002.002ዳን፥ ዮሴፍ፥ ብንያም፥ ንፍታሌም፥ ጋድ፥ አሴር።
2:3b.1CH.002.003የይሁዳ ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም፤ እነዚህ ሦስቱ ከከነዓናዊቱ ከሴዋ ልጅ ተወለዱለት። የይሁዳም የበኵር ልጅ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ ገደለውም።
2:4b.1CH.002.004ምራቱም ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ የይሁዳም ልጆች ሁሉ አምስት ነበሩ።
2:5b.1CH.002.005የፋሬስ ልጆች፤ ኤስሮም፥ ሐሙል።
2:6b.1CH.002.006የዛራም ልጆች፤ ዘምሪ፥ ኤታን፥ ሄማን፥
2:7b.1CH.002.007ከልኮል፥ ዳራ፤ ሁሉም አምስት ነበሩ። የከርሚም ልጅ እስራኤልን ያስጨነቀ፥ እርሙንም ሰርቆ የበደለ አካን ነበረ።
2:8b.1CH.002.008የኤታንም ልጅ አዛርያ ነበረ።
2:9b.1CH.002.009ለኤስሮም የተወለዱለት ልጆች፤ ይረሕምኤል፥ አራም፥ ካልብ ነበሩ።
2:10b.1CH.002.010አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም የይሁዳን ልጆች አለቃ ነአሶንን ወለደ፤
2:11b.1CH.002.011ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞንም ቦዔዝን ወለደ፤
2:12b.1CH.002.012ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤
2:13b.1CH.002.013እሴይም የበኵር ልጁን ኤልያብን፥ ሁለተኛውንም አሚናዳብን፥ ሦስተኛውንም ሣማን፥
2:14b.1CH.002.014አራተኛውንም ናትናኤልን፥
2:15b.1CH.002.015አምስተኛውንም ራዳይን፥ ስድስተኛውንም አሳምን፥ ሰባተኛውንም ዳዊትን ወለደ፤
2:16b.1CH.002.016እኅቶቻቸውም ጽሩያና አቢግያ ነበሩ። የጽሩያም ልጆች አቢሳ፥ ኢዮአብ፥ አሣሄል ሦስቱ ነበሩ።
2:17b.1CH.002.017አቢግያም አሜሳይን ወለደች፤ የአሜሳይም አባት እስማኤላዊው ዬቴር ነበረ።
2:18b.1CH.002.018የኤስሮምም ልጅ ካሌብ ከሚስቱ ከዓዙባ ከይሪዖትም ልጆች ወለደ፤ ልጆቹዋም ያሳር፥ ሶባብ፥ አርዶን ነበሩ።
2:19b.1CH.002.019ዓዙባም ሞተች፥ ካሌብም ኤፍራታን አገባ፤ እርስዋም ሆርን ወለደችለት።
2:20b.1CH.002.020ሆርም ኡሪን ወለደ፥ ኡሪም ባስልኤልን ወለደ።
2:21b.1CH.002.021ከዚያም በኋላ ኤስሮም ስድሳ ዓመት በሆነው ጊዜ ወዳገባት ወደ ገለዓድ አባት ወደ ማኪር ልጅ ገባ፤ ሠጉብንም ወለደችለት። ሠጉብም ኢያዕርን ወለደ፤
2:22b.1CH.002.022ለእርሱም በገለዓድ ምድር ሀያ ሦስት ከተሞች ነበሩት።
2:23b.1CH.002.023ጌሹርና አራምም የኢያዕርን ከተሞች ከቄናትና ከመንደሮችዋ ጋር ስድሳውን ከተሞች ወሰዱባቸው። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ልጆች ነበሩ።
2:24b.1CH.002.024ኤስሮምም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ የኤስሮም ሚስት አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።
2:25b.1CH.002.025የኤስሮምም የበኵር ልጁ የይረሕምኤል ልጆች በኵሩ ራም፥ ቡናህ፥ ኦሬን፥ ኦጼም፥ አኪያ ነበሩ።
2:26b.1CH.002.026ለይረሕምኤልም ዓጣራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው፤ እርስዋም የኦናም እናት ነበረች።
2:27b.1CH.002.027የይረሕምኤል የበኵሩ የራም ልጆች መዓስ፥ ያሚን፥ ዔቄር ነበሩ።
2:28b.1CH.002.028የኦናምም ልጆች ሸማይና ያዳ ነበሩ። የሸማይ ልጆች ናዳብና አቢሱር ነበሩ።
2:29b.1CH.002.029የአቢሱርም ሚስት አቢካኢል ነበረች፤ አሕባንንና ሞሊድን ወለደችለት።
2:30b.1CH.002.030የናዳብም ልጆች ሴሊድና አፋይም ነበሩ፤ ሴሌድም ያለ ልጆች ሞተ።
2:31b.1CH.002.031የአፋይምም ልጅ ይሽዒ፥ የይሽዒም ልጅ ሶሳን፥ የሶሳንም ልጅ አሕላይ ነበረ።
2:32b.1CH.002.032የሸማይም ወንድም የያዳ ልጆች ዬቴርና ዮናታን ነበሩ፤ ዬቴርም ያለ ልጆች ሞተ።
2:33b.1CH.002.033የዮናታንም ልጆች ፌሌትና ዛዛ ነበሩ፤ እነዚህ የይረሕምኤል ልጆች ነበሩ።
2:34b.1CH.002.034ለሶሳንም ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ለሶሳንም ኢዮሄል የተባለ ግብጻዊ አገልጋይ ነበረው።
2:35b.1CH.002.035ሶሳንም ለአገልጋዩ ለኢዮሄል ልጁን አጋባት፥ እርስዋም ዓታይን ወለደችለት።
2:36b.1CH.002.036ዓታይም ናታንን ወለደ፤ ናታንም ዛባድን ወለደ፤
2:37b.1CH.002.037ዛባድም ኤፍላልን ወለደ፤ ኤፍላልም ዖቤድን ወለደ፤ ዖቤድም ኢዩን ወለደ፤
2:38b.1CH.002.038ኢዩም ዓዛርያስን ወለደ፤
2:39b.1CH.002.039ዓዛርያስም ኬሌስን ወለደ፤ ኬሌስም ኤልዓሣን ወለደ፤
2:40b.1CH.002.040ኤልዓሣም ሲስማይን ወለደ፤
2:41b.1CH.002.041ሲስማይም ሰሎምን ወለደ፤ ሰሎምም የቃምያን ወለደ፤ የቃምያም ኤሊሳማን ወለደ።
2:42b.1CH.002.042የይረሕምኤልም ወንድም የካሌብ ልጆች በኵሩ የዚፍ አባት ሞሳ፥ የኬብሮንም አባት የመሪሳ ልጆች ነበሩ።
2:43b.1CH.002.043የኬብሮንም ልጆች ቆሬ፥ ተፉዋ፥ ሬቄም፥ ሽማዕ ነበሩ።
2:44b.1CH.002.044ሽማዕም የዮርቅዓምን አባት ረሐምን ወለደ፤ ሬቄምም ሸማይን ወለደ።
2:45b.1CH.002.045የሸማይም ልጅ ማዖን ነበረ፤ ማዖንም የቤት ጹር አባት ነበረ።
2:46b.1CH.002.046የካሌብም ቁባት ዔፋ ሐራንን፥ ሞዳን፥ ጋዜዝን ወለደች።
2:47b.1CH.002.047ሐራንም ጋዜዝን ወለደ። የያህዳይም ልጆች ሬጌም፥ ኢዮታም፥ ጌሻን፥ ፋሌጥ፥ ሔፋ፥ ሸዓፍ ነበሩ።
2:48b.1CH.002.048የካሌብም ቁባት ማዕካ ሸቤርንና ቲርሐናን ወለደች።
2:49b.1CH.002.049ደግሞም የመድማናን አባት ሸዓፍንና የመክቢናንና የጊብዓን አባት ሱሳን ወለደች፤ የካሌብም ሴት ልጅ ዓክሳ ነበረች።
2:50b.1CH.002.050የካሌብ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የኤፍራታ የበኵሩ የሆር ልጅ የቂርያትይዓሪም አባት ሦባል፥
2:51b.1CH.002.051የቤተ ልሔም አባት ሰልሞን፥ የቤት ጋዴር አባት ሐሬፍ።
2:52b.1CH.002.052ለቂርያትይዓሪምም አባት ለሦባል ልጆች ነበሩት፤ ሀሮኤ የመናሕታውያን እኵሌታ።
2:53b.1CH.002.053የቂርያትይዓሪምም ወገኖች፤ ይትራውያን፥ ፉታውያን፥ ሹማታውያን፥ ሚሽራውያን፤ ከእነዚህም ጾርዓውያንና ኤሽታኦላውያን ወጡ።
2:54b.1CH.002.054የሰልሞንም ልጆች ቤተ ልሔም፥ ነጦፋውያን፥ ዓጣሮትቤትዮአብ፥ የመናሕታውያን እኵሌታ፥ ጾርዓውያን ነበሩ።
2:55b.1CH.002.055በያቤጽም የተቀመጡ የጸሐፊዎች ወገኖች፤ ቲርዓውያን፥ ሺምዓታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው።
3
3:1b.1CH.003.001በኬብሮንም ለዳዊት የተወለዱለት ልጆች እነዚህ ናቸው። በኵሩ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም፥ ሁለተኛውም ዳንኤል ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቢግያ፥
3:2b.1CH.003.002ሦስተኛው አቤሴሎም ከጌሹር ንጉሥ ከተልማይ ልጅ ከመዓካ፥ አራተኛው አዶንያስ ከአጊት፥
3:3b.1CH.003.003አምስተኛው ሰፋጥያስ ከአቢጣል፥ ስድስተኛው ይትረኃም ከሚስቱ ከዔግላ።
3:4b.1CH.003.004ስድስቱ በኬብሮን ተወለዱለት፤ በዚያም ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ።
3:5b.1CH.003.005እነዚህ ደግሞ በኢየሩሳሌም ተወለዱለት፤ ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ፥ ሳሙስ፥ ሶባብ፥ ናታን፥
3:6b.1CH.003.006ሰሎሞን፥ አራት፤ ኢያቤሐር፥ ኤሊሱዔ፥
3:7b.1CH.003.007ኤሊፋላት፥ ኖጋ፥ ናፌቅ፥ ያፍያ፥
3:8b.1CH.003.008ኤሊሳማ፥ ኤሊዳሄ፥ ኤሊፋላት፥ ዘጠኝ።
3:9b.1CH.003.009እነዚህ ሁሉ ከቁባቶች ልጆች በቀር የዳዊት ልጆች ነበሩ፤ ትዕማርም እኅታቸው ነበረች።
3:10b.1CH.003.010የሰሎሞንም ልጅ ሮብዓም ነበረ፤ ልጁ አቢያ፥
3:11b.1CH.003.011ልጁ አሳ፥ ልጁ ኢዮሣፍጥ፥ ልጁ ኢዮራም፥ ልጁ አካዝያስ፥ ልጁ ኢዮአስ፥
3:12b.1CH.003.012ልጁ አሜስያስ፥ ልጁ ዓዛርያስ፥ ልጁ ኢዮአታም፥
3:13b.1CH.003.013ልጁ አካዝ፥ ልጁ ሕዝቅያስ፥ ልጁ ምናሴ፥
3:14b.1CH.003.014ልጁ አሞጽ፥ ልጁ ኢዮስያስ።
3:15b.1CH.003.015የኢዮስያስም ልጆች፤ በኵሩ ዮሐናን፥ ሁለተኛውም ኢዮአቄም፥ ሦስተኛውም ሴዴቅያስ፥ አራተኛውም ሰሎም።
3:16b.1CH.003.016የኢዮአቄምም ልጆች፤ ልጁ ኢኮንያን፥ ልጁ ሴዴቅያስ።
3:17b.1CH.003.017የምርኮኛውም የኢኮንያን ልጆች ሰላትያል፥ መልኪራም፥
3:18b.1CH.003.018ፈዳያ፥ ሼናጻር፥ ይቃምያ፥ ሆሻማ፥ ነዳብያ ነበሩ።
3:19b.1CH.003.019የፈዳያ ልጆች ዘሩባቤልና ሰሜኢ ነበሩ፤ የዘሩባቤልም ልጆች፤ ሜሱላም፥ ሐናንያ፥ እኅታቸውም ሰሎሚት።
3:20b.1CH.003.020ሐሹባ፥ ኦሄል፥ በራክያ፥ ሐሳድያ፥ ዮሻብሒሴድ አምስት ናቸው።
3:21b.1CH.003.021የሐናንያም ልጆች ፈላጥያና የሻያ ነበሩ። የረፋያ ልጆች፥ የአርናን ልጆች፥ የአብድዩ ልጆች፥ የሴኬንያ ልጆች።
3:22b.1CH.003.022የሴኬንያም ልጅ ሸማያ ነበረ። የሸማያም ልጆች ሐጡስ፥ ይግኣል፥ ባርያሕ፥ ነዓርያ፥ ሻፋጥ ስድስት ነበሩ።
3:23b.1CH.003.023የነዓርያም ልጆች ኤልዮዔናይ፥ ሕዝቅያስ፥ ዓዝሪቃም ሦስት ነበሩ።
3:24b.1CH.003.024የኤልዮዔናይም ልጆች ሆዳይዋ፥ ኤልያሴብ፥ ፌልያ፥ ዓቁብ፥ ዮሐናን፥ ደላያ፥ ዓናኒ ሰባት ነበሩ።
4
4:1b.1CH.004.001የይሁዳ ልጆች ፋሬስ፥ ኤስሮም፥ ከርሚ፥ ሆር፥ ሦባል ናቸው።
4:2b.1CH.004.002የሦባልም ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤትም አሑማይንና ላሃድን ወለደ። እነዚህ የጾርዓውያን ወገኖች ናቸው።
4:3b.1CH.004.003እነዚህም የኤጣም አባት ልጆች ናቸው፤ ኢይዝራኤል፥ ይሽማ፥ ይድባሽ፥ እኅታቸውም ሃጽሌልፎኒ።
4:4b.1CH.004.004የጌዶርም አባት ፋኑኤል፥ የሑሻም አባት ኤጽር፤ እነዚህ የቤተ ልሔም አባት የኤፍራታ የበኵሩ የሆር ልጆች ናቸው።
4:5b.1CH.004.005ለቴቁሔም አባት ለአሽሑር ሔላና ነዕራ የተባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት።
4:6b.1CH.004.006ነዕራም አሑዛምን፥ ኦፌርን፥ ቴምኒን፥ አሐሽታሪን ወለደችለት። እነዚህ የነዕራ ልጆች ናቸው።
4:7b.1CH.004.007የሔላም ልጆች ዴሬት፥ ይጽሐር፥ ኤትናን ናቸው።
4:8b.1CH.004.008ቆጽ ዓኑብን፥ ጾቤባን፥ የሃሩምንም ልጅ የአሐርሔልን ወገኖች ወለደ።
4:9b.1CH.004.009ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም። በጣር ወልጄዋለሁና ብላ ስሙን። ያቤጽ ብላ ጠራችው።
4:10b.1CH.004.010ያቤጽም። እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
4:11b.1CH.004.011የሹሐም ወንድም ክሉብ የኤሽቶንን አባት ምሒርን ወለደ።
4:12b.1CH.004.012ኤሽቶንም ቤትራ ፋንና ፋሴሐን የዒርናሐሽንም አባት ተሒናን ወለደ፤ እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው።
4:13b.1CH.004.013የቄኔዝም ልጆች ጎቶንያልና ሠራያ ነበሩ። የጎቶንያልም ልጅ ሐታት ነበረ።
4:14b.1CH.004.014መዖኖታይ ዖፍራን ወለደ። ሠራያም የጌሃራሽምን አባት ኢዮአብን ወለደ፤ እነርሱም ጠራቢዎች ነበሩ።
4:15b.1CH.004.015የዮፎኒም ልጅ የካሌብ ልጆች ዒሩ፥ ኤላ፥ ነዓም ነበሩ።
4:16b.1CH.004.016የኤላም ልጅ ቄኔዝ ነበረ። የይሃሌልኤል ልጆች ዚፍ፥ ዚፋ፥ ቲርያ፥ አሣርኤል ነበሩ።
4:17b.1CH.004.017የዕዝራም ልጆች ዬቴር፥ ሜሬድ፥ ዔፌር፥ ያሎን ነበሩ፤ ዬቴርም ማርያምን፥ ሸማይን፥ የኤሽትምዓን አባት ይሽባን ወለደ።
4:18b.1CH.004.018አይሁዳዊቱም ሚስቱ የጌዶርን አባት ዬሬድን፥ የሦኮንም አባት ሔቤርን፥ የዛኖዋንም አባት ይቁቲኤልን ወለደች። እነዚህም ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።
4:19b.1CH.004.019የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ልጆች የገርሚው የቅዒላ አባትና ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ ነበሩ።
4:20b.1CH.004.020የሺሞንም ልጆች አምኖን፥ ሪና፥ ቤንሐናን፥ ቲሎን ነበሩ። የይሽዒም ልጆች ዞሔትና ቢንዞሔት ነበሩ።
4:21b.1CH.004.021የይሁዳም ልጅ የሴሎም ልጆች የሌካ አባት ዔር፥ የመሪሳ አባት ለዓዳ፥ ከአሽቤዓ ቤት የሚሆኑ ጥሩ በፍታ የሚሠሩ ወገኖች፥
4:22b.1CH.004.022ዮቂም፥ የኮዜባ ሰዎች፥ ኢዮአስ፥ ሞዓብን የገዛ ሣራፍ፥ ያሹቢሌሔም ነበሩ።
4:23b.1CH.004.023ይህ ዝና ከቀድሞ ጀምሮ ነበረ። እነዚህ በነጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠራተኞች ነበሩ። በዚያ በንጉሡ ዘንድ ስለ ሥራው ይቀመጡ ነበር።
4:24b.1CH.004.024የስምዖንም ልጆች፤ ነሙኤል፥ ያሚን፥ ያሪን፥ ዛራ፥ ሳኡል፤
4:25b.1CH.004.025ልጁ ሰሎም፥ ልጁ መብሳም፥ ልጁ ማስማዕ።
4:26b.1CH.004.026የማስማዕም ልጆች፤ ልጁ ሃሙኤል፥ ልጁ ዘኩር፥ ልጁ ሰሜኢ።
4:27b.1CH.004.027ለሰሜኢም አሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ለወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልነበሩአቸውም፥ ወገናቸውም ሁሉ እንደ ይሁዳ ልጆች አልተባዙም።
4:28b.1CH.004.028በቤርሳቤህም፥ በሞላዳ፥
4:29b.1CH.004.029በሐጸርሹዓል፥ በቢልሃ፥ በዔጼም፥
4:30b.1CH.004.030በቶላድ፥ በቤቱኤል፥ በሔርማ፥ በጺቅላግ፥
4:31b.1CH.004.031በቤትማርካቦት፥ በሐጸርሱሲም፥ በቤትቢሪ፥ በሸዓራይም ይቀመጡ ነበር። እስከ ዳዊትም መንግሥት ድረስ ከተሞቻቸው እነዚህ ነበሩ።
4:32b.1CH.004.032መንደሮቻቸውም ኤጣም፥ ዓይን፥ ሬሞን፥ ቶኬን፥ ዓሻን፥ አምስቱ ከተሞች፤
4:33b.1CH.004.033እስከ በኣልም ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ የነበሩ መንደሮቻቸው ሁሉ ነበሩ። መቀመጫቸውና የትውልዳቸው መዝገቦች እነዚህ ናቸው።
4:34b.1CH.004.034ምሾባብ፥ የምሌክ፥ የአሜስያስ ልጅ ኢዮስያ፥
4:35b.1CH.004.035ኢዮኤል፥ የዮሺብያ ልጅ፥ የሠራያ ልጅ የዓሢኤል ልጅ ኢዩ፥
4:36b.1CH.004.036ኤልዮዔናይ፥ ያዕቆባ፥ የሾሐያ፥ ዓሣያ፥ ዓዲዔል፥ ዩሲምኤል፥ በናያስ፥
4:37b.1CH.004.037የሺፊ ልጅ ዚዛ፥ የአሎን ልጅ የይዳያ ልጅ የሺምሪ ልጅ የሸማያ ልጅ፤
4:38b.1CH.004.038እነዚህ በስማቸው የተጠሩ በወገኖቻቸው ላይ አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸውም ቤቶች በዝተው ነበር።
4:39b.1CH.004.039ለመንጎቻቸው መሰምርያ ይሹ ዘንድ ወደ ጌዶር መግቢያ እስከ ሸለቆው ምሥራቅ ድረስ ሄዱ።
4:40b.1CH.004.040የለመለመችም እጅግም ያማረች መሰምርያ አገኙ፤ ምድሪቱም ሰፊና ጸጥተኛ ሰላም ያላትም ነበረች፤ በቀድሞም ጊዜ በዚያ ተቀምጠው የነበሩ ከካም ወገን ነበሩ።
4:41b.1CH.004.041እነዚህም በስማቸው የተጻፉ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰምርያ ነበረና በስፍራቸው ተቀመጡ።
4:42b.1CH.004.042የስምዖንም ልጆች አምስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ፤ አለቆቻቸውም የይሽዒ ልጆች፥ ፈላጥያ፥ ነዓርያ፥ ረፋያ፥ ዑዝኤል ነበሩ።
4:43b.1CH.004.043ያመለጡትንም የአማሌቃውያንን ቅሬታ መቱ፥ በዚያም እስከ ዛሬ ድረስ ተቀምጠዋል።
5
5:1b.1CH.005.001የእስራኤልም በኵር የሮቤል ልጆች እነዚህ ናቸው። እርሱ የበኵር ልጅ ነበረ፤ ነገር ግን የአባቱን ምንጣፍ ስላረከሰ ብኵርናው ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጠ፤ ትውልዱ ግን ከብኵርና ጋር አልተቈጠረም።
5:2b.1CH.005.002ይሁዳም በወንድሞቹ መካከል በረታ፥ አለቃም ከእርሱ ሆነ፤ ብኵርናው ግን ለዮሴፍ ነበረ።
5:3b.1CH.005.003የእስራኤል በኵር የሮቤል ልጆች፤ ሄኖኅ፥ ፈሉሶ፥ አስሮን፥ ከርሚ ነበሩ።
5:4b.1CH.005.004የኢዮኤል ልጆች፤ ልጁ ሸማያ፥
5:5b.1CH.005.005ልጁ ጎግ፥ ልጁ ሰሜኢ፥ ልጁ ሚካ፥
5:6b.1CH.005.006ልጁ ራያ፥ ልጁ ቢኤል፥ የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር የማረከው ልጁ ብኤራ፤ እርሱ የሮቤል ነገድ አለቃ ነበረ።
5:7b.1CH.005.007ወንድሞቹ በየወገናቸው የትውልዶቻቸው መዝገብ በተቈጠረ ጊዜ፤ አንደኛው ኢዮኤል፥
5:8b.1CH.005.008ዘካርያስ፥ እስከ ናባውና እስከ በኣልሜዎን ድረስ በአሮዔር የተቀመጠው የኢዮኤል ልጅ የሽማዕ ልጅ የዖዛዝ ልጅ ቤላ፤
5:9b.1CH.005.009በገለዓድ ምድር እንስሶቻቸው በዝተው ነበርና በምሥራቅ በኩል ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምድረ በዳው መግቢያ ድረስ ተቀመጠ።
5:10b.1CH.005.010በሳኦልም ዘመን ከአጋራውያን ጋር ተዋጉ፥ እነርሱም በእጃቸው ተመትተው ወደቁ፤ በገለዓድ ምሥራቅ በኩል ባለው አገር ሁሉ በድንኳኖቻቸው ተቀመጡ።
5:11b.1CH.005.011የጋድም ልጆች በባሳን ምድር እስከ ሰልካ ድረስ በአፋዛዣቸው ተቀመጡ።
5:12b.1CH.005.012አንደኛው ኢዮኤል፥ ሁለተኛው ሳፋም፥ ያናይ፥ ሳፋጥ በበሳን ተቀመጡ።
5:13b.1CH.005.013የአባቶቻቸውም ቤቶች ወንድሞች ሚካኤል፥ ሜሱላም፥ ሳባ፥ ዮራይ፥ ያካን፥ ዙኤ፥ ኦቤድ ሰባት ነበሩ።
5:14b.1CH.005.014እነዚህም የቡዝ ልጅ የዬዳይ ልጅ የኢዬሳይ ልጅ የሚካኤል ልጅ የገለዓድ ልጅ የኢዳይ ልጅ የዑሪ ልጅ የአቢካኢል ልጆች ነበሩ።
5:15b.1CH.005.015የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቃ የጉኒ ልጅ የአብዲኤል ልጅ ወንድም ነበረ።
5:16b.1CH.005.016በገለዓድም ምድር በባሳን በመንደሮቹም በሳሮንም መሰምርያዎች ሁሉ እስከ ዳርቻቸው ድረስ ተቀምጠው ነበር።
5:17b.1CH.005.017እነዚህ ሁሉ በትውልዶቻቸው በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአታም ዘመንና በእስራኤል ንጉሥ በኢዮርብዓም ዘመን ተቈጠሩ።
5:18b.1CH.005.018የሮቤልና የጋድ ልጆች የምናሴም ነገድ እኵሌታ፥ ጽኑዓን፥ ጋሻና ሰይፍ የሚይዙ፥ ቀስተኞችም፥ ሰልፍ የሚያውቁ ሰልፈኞችም፥ አርባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ነበሩ።
5:19b.1CH.005.019ከአጋራውያንና ከኢጡር ከናፌስና ከናዳብ ጋር ተዋጉ።
5:20b.1CH.005.020በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና፥ በእርሱም ታምነዋልና ተለመናቸው፤ በላያቸውም ረዳት ሆናቸው፥ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተሰጡ።
5:21b.1CH.005.021ከከብቶቻቸውም አምሳ ሺህ ግመሎች፥ ሁለት መቶ አምሳ ሺህም በጎች፥ ሁለት ሺህም አህዮች፥ ከሰዎችም መቶ ሺህ ማረኩ።
5:22b.1CH.005.022ሰልፉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነበረና ብዙ ሰዎች ተገድለው ወደቁ፤ እስከ ምርኮም ዘመን ድረስ በስፍራቸው ተቀመጡ።
5:23b.1CH.005.023የምናሴ የነገድ እኵሌታ ልጆች በምድሪቱ ተቀመጡ። ከባሳንም ጀምሮ እስከ በኣልአርሞንዔምና እስከ ሳኔር እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በዙ።
5:24b.1CH.005.024የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፥ ይሽዒ፥ ኤሊኤል፥ ዓዝርኤል፥ ኤርምያ፥ ሆዳይዋ፥ ኢየድኤል፤ እነርሱ ጽኑዓን ኃያላን የታወቁ ሰዎች የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች ነበሩ።
5:25b.1CH.005.025የአባቶቻቸውንም አምላክ በደሉ፥ እግዚአብሔርም ከፊታቸው ባጠፋቸው በምድሩ አሕዛብ አማልክት አመነዘሩ።
5:26b.1CH.005.026የእስራኤልም አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፎሐን መንፈስ፥ የአሦርንም ንጉሥ የቴልጌልቴልፌልሶርን መንፈስ አስነሣ፤ የሮቤልንና የጋድን ልጆች የምናሴንም ነገድ እኵሌታ አፈለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳሉበት ወደ አላሔና ወደ ኦቦር፥ ወደ ሃራና ወደ ጎዛን ወንዝ አመጣቸው።
6
6:1b.1CH.006.001የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።
6:2b.1CH.006.002የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል።
6:3b.1CH.006.003የእንበረምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም። የአሮን ልጆች፤ ናዳብ፥ አብዮድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር።
6:4b.1CH.006.004አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤
6:5b.1CH.006.005አቢሱም ቡቂን ወለደ፤ ቡቂም ኦዚን ወለደ፤
6:6b.1CH.006.006ኦዚም ዘራእያን ወለደ፤ ዘራእያም መራዮትን ወለደ፤
6:7b.1CH.006.007መራዮት አማርያን ወለደ፤
6:8b.1CH.006.008አማርያም አኪጦብን ወለደ፤ አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪማአስን ወለደ፤
6:9b.1CH.006.009አኪማአስም ዓዛርያስን ወለደ፤
6:10b.1CH.006.010ዓዛርያስም ዮሐናንን ወለደ፤ ዮሐናንም ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም በሠራው ቤት ካህን ነበረ፤
6:11b.1CH.006.011ዓዛርያስም አማርያን ወለደ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤
6:12b.1CH.006.012አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም ሰሎምን ወለደ፤
6:13b.1CH.006.013ሰሎምም ኬልቅያስን ወለደ፤ ኬልቅያስም ዓዛርያስን ወለደ፤
6:14b.1CH.006.014ዓዛርያስም ሠራያን ወለደ፤ ሠራያም ኢዮሴዴቅን ወለደ፤
6:15b.1CH.006.015እግዚአብሔርም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን በናቡከደነፆር እጅ ባስማረከ ጊዜ ኢዮሴዴቅ ተማርኮ ሄደ።
6:16b.1CH.006.016የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።
6:17b.1CH.006.017የጌድሶንም ልጆች ስም ይህ ነው፤ ሎቤኒ ሰሜኢ።
6:18b.1CH.006.018የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል ነበሩ።
6:19b.1CH.006.019የሜራሪ ልጆች፤ ሞሖሊም፥ ሙሲ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው።
6:20b.1CH.006.020ከጌድሶን፤ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ኢኤት፥ ልጁ ዛማት፥
6:21b.1CH.006.021ልጁ ዮአክ፥ ልጁ አዶ፥ ልጁ ዛራ፥ ልጁ ያትራይ።
6:22b.1CH.006.022የቀዓት ልጆች፤ ልጁ አሚናዳብ፥
6:23b.1CH.006.023ልጁ ቆሬ፥ ልጁ አሴር፥ ልጁ ሕልቃና፥
6:24b.1CH.006.024ልጁ አቢሳፍ፥ ልጁ አሴር፥ ልጁ ኢኢት፥ ልጁ ኡሩኤል፥ ልጁ ዖዝያ፥ ልጁ ሳውል።
6:25b.1CH.006.025የሕልቃናም ልጆች፤ አማሢ፥ አኪሞት።
6:26b.1CH.006.026የሕልቃናም ልጆች፤ ልጁ ሱፊ፥
6:27b.1CH.006.027ልጁ ናሐት፥ ልጁ ኤልያብ፥ ልጁ ይሮሐም፥ ልጁ ሕልቃና።
6:28b.1CH.006.028የሳሙኤልም ልጆች፤ በኵሩ ኢዮኤል፥ ሁለተኛውም አብያ።
6:29b.1CH.006.029የሜራሪ ልጆች፤ ሞሖሊ፥ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ሰሜኢ፥
6:30b.1CH.006.030ልጁ ዖዛ፥ ልጁ ሳምዓ፥ ልጁ ሐግያ፥ ልጁ ዓሣያ።
6:31b.1CH.006.031ዳዊትም ታቦቱ ዐርፎ ከተቀመጠ በኋላ በእግዚአብሔር ቤት ያቆማቸው የመዘምራን አለቆች እነዚህ ናቸው።
6:32b.1CH.006.032ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ያገለግሉ ነበር።
6:33b.1CH.006.033አገልጋዮቹና ልጆቹ እነዚህ ናቸው፤ ከቀዓት ልጆች ዘማሪው ኤማን ነበረ፤ እርሱም የኢዮኤል ልጅ፥
6:34b.1CH.006.034የሳሙኤል ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፥
6:35b.1CH.006.035የሱፍ ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የመሐት ልጅ፥
6:36b.1CH.006.036የአማሢ ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የኢዮኤል ልጅ፥ የዓዛርያስ ልጅ፥ የሶፎንያስ ልጅ፥
6:37b.1CH.006.037የታሐት ልጅ፥ የአሴር ልጅ፥
6:38b.1CH.006.038የአብያሳፍ ልጅ፥ የቆሬ ልጅ፥ የይስዓር ልጅ፥ የቀዓት ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ የእስራኤል ልጅ ነው።
6:39b.1CH.006.039በቀኙም የቆመ ወንድሙ አሳፍ ነበረ፤ አሳፍም የበራክያ ልጅ፥
6:40b.1CH.006.040የሳምዓ ልጅ፥ የሚካኤል ልጅ፥ የበዓሤያ ልጅ፥
6:41b.1CH.006.041የመልክያ ልጅ፥ የኤትኒ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥
6:42b.1CH.006.042የዓዳያ ልጅ፥ የኤታን ልጅ፥ የዛማት ልጅ፥
6:43b.1CH.006.043የሰሜኢ ልጅ፥ የኢኤት ልጅ፥ የጌድሶን ልጅ፥ የሌዊ ልጅ ነው።
6:44b.1CH.006.044በግራቸውም በኩል ወንድሞቻቸው የሜራሪ ልጆች ነበሩ፤ ኤታን የቂሳ ልጅ፥ የአብዲ ልጅ፥
6:45b.1CH.006.045የማሎክ ልጅ፥ የሐሸብያ ልጅ፥ የአሜስያስ ልጅ፥
6:46b.1CH.006.046የኬልቅያስ ልጅ፥ የአማሲ ልጅ፥
6:47b.1CH.006.047የባኒ ልጅ፥ የሴሜር ልጅ፥ የሞሖሊ ልጅ፥ የሙሲ ልጅ፥ የሜራሪ ልጅ፥ የሌዊ ልጅ።
6:48b.1CH.006.048ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ቤት ማደሪያ አገልግሎት ሁሉ ተሰጡ።
6:49b.1CH.006.049አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአሔር ባሪያ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ያስተሰርይ ዘንድ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር።
6:50b.1CH.006.050የአሮንም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ልጁ አልዓዛር፥
6:51b.1CH.006.051ልጁ ፊንሐስ፥ ልጁ አቢሱ፥ ልጁ ቡቂ፥
6:52b.1CH.006.052ልጁ ኦዚ፥ ልጁ ዘራእያ፥ ልጁ መራዮት፥
6:53b.1CH.006.053ልጁ አማርያ፥ ልጁ አኪጦብ፥ ልጁ ሳዶቅ፥ ልጁ አኪማአስ።
6:54b.1CH.006.054ማደሪያዎቻቸውም በየሰፈራቸው በየዳርቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ለአሮን ልጆች ለቀዓት ወገኖች አንደኛው ዕጣ ነበረ።
6:55b.1CH.006.055ለእነርሱ በይሁዳ አገር ያለችውን ኬብሮንን፥ በእርስዋም ዙሪያ የነበረውን መሰምርያ ሰጡ፤
6:56b.1CH.006.056የከተማይቱን እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ሰጡ።
6:57b.1CH.006.057ለአሮንም ልጆች የመማፀኛውን ከተሞች፥ ኬብሮንን፥ ልብናንና መሰምርያዋን፥ ደግሞ የቲርን፥
6:58b.1CH.006.058ኤሽትሞዓንና መሰምርያዋን፥ ሖሎንንና መሰምርያዋን፥ ዳቤርንና መሰምርያዋን፥
6:59b.1CH.006.059ዓሳንንና መሰምርያዋን፥ ቤትሳሚስንና መሰምርያዋን፤
6:60b.1CH.006.060ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰምርያዋን፥ ጋሌማትንና መሰምርያዋን፥ ዓናቶትንና መሰምርያዋን ሰጡ። ከተሞቻተው ሁሉ በየወገናቸው አሥራ ሦስት ነበሩ።
6:61b.1CH.006.061ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከነገዱ ወገን ከምናሴ ነገድ እኵሌታ አሥር ከተሞች በዕጣ ተሰጡ።
6:62b.1CH.006.062ለጌድሶንም ልጆች በየወገናቸው ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ፥ አሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጡ።
6:63b.1CH.006.063ለሜራሪ ልጆች በየወገናቸው ከሮቤል ነገድ፥ ከጋድም ነገድ፥ ከዛብሎንም ነገድ፥ አሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተሰጡ።
6:64b.1CH.006.064የእስራኤልም ልጆች ለሌዋውያን ከተሞችን ከመሰምርያዎቻቸው ጋር ሰጡ።
6:65b.1CH.006.065ከይሁዳም ልጆች ነገድ፥ ከስምዖንም ልጆች ነገድ፥ ከብንያምም ልጆች ነገድ፥ እነዚህን በስማቸው የተጠሩትን ከተሞች በዕጣ ሰጡ።
6:66b.1CH.006.066ከቀዓትም ልጆች ወገኖች ለአንዳንዶቹ ከኤፍሬም ነገድ ከተሞች ድርሻ ነበራቸው።
6:67b.1CH.006.067በተራራማው በኤፍሬም አገር ያሉትን የመማፀኛውን ከተሞች ሴኬምንና መሰምርያዋን፥ ደግሞም ጌዝርንና መሰምርያዋን፥ ዮቅምዓምንና መሰምርያዋን፥
6:68b.1CH.006.068ቤትሖሮንንና መሰምርያዋን፥
6:69b.1CH.006.069ኤሎንንና መሰምርያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰምርያዋን ሰጡአቸው።
6:70b.1CH.006.070ከምናሴም ነገድ እኵሌታ ዓኔርንና መሰምርያዋን፥ ቢልዓምንና መሰምርያዋን ከቀዓት ልጆች ወገን ለቀሩት ሰጡ።
6:71b.1CH.006.071ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኵሌታ ወገን በባሳን ያለችው ጎላንና መሰምርያዋ፥ አስታሮትና መሰምርያዋ፤
6:72b.1CH.006.072ከይሳኮርም ነገድ ቃዴስና መሰምርያዋ፥ ዳብራትና መሰምርያዋ፥
6:73b.1CH.006.073ራሞትና መሰምርያዋ፥ ዓኔምና መሰምርያዋ፤
6:74b.1CH.006.074ከአሴርም ነገድ መዓሳልና መሰምርያዋ፥ ዓብዶንና መሰምርያዋ፥
6:75b.1CH.006.075ሑቆቅና መሰምርያዋ፥ ረአብና መሰምርያዋ፤
6:76b.1CH.006.076ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰምርያዋ፥ ሐሞንና መሰምርያዋ፥ ቂርያታይምና መሰምርያዋ ተሰጡ።
6:77b.1CH.006.077ከሌዋውያን ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ከዛብሎን ነገድ ሬሞንና መሰምርያዋ፥ ታቦርና መሰምርያዋ፤
6:78b.1CH.006.078ከሮቤልም ነገድ በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል በምድረ በዳ ያለችው ቦሶርና መሰምርያዋ፥
6:79b.1CH.006.079ያሳና መሰምርያዋ፥ ቅዴሞትና መሰምርያዋ፥ ሜፍዓትና መሰምርያዋ፤
6:80b.1CH.006.080ከጋድም ነገድ በገለዓድ ያለችው ሬማትና መሰምርያዋ፥ መሃናይምና መሰምርያዋ፥
6:81b.1CH.006.081ሐሴቦንና መሰምርያዋ፥ ኢያዜርና መሰምርያዋ ተሰጡ።
7
7:1b.1CH.007.001የይሳኮርም ልጆች፥ ቶላ፥ ፉዋ፥ ያሱብ ሺምሮን፥ አራት ናቸው።
7:2b.1CH.007.002የቶላም ልጆች፥ ኦዚ፥ ራፋያ፥ ይሪኤል፥ የሕማይ፥ ይብሣም፥ ሽሙኤል፥ የአባታቸው የቶላ ቤት አለቆች፥ በትውልዳቸው ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ፤ በዳዊት ዘመን ቍጥራቸው ሀያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበረ።
7:3b.1CH.007.003የኦዚም ልጆች ይዝረሕያ፤ የይዝረሕያም ልጆች ሚካኤል፥ አብድዩ፥ ኢዮኤል፥ ይሺያ አምስት ናቸው፤ ሁሉም አለቆች ነበሩ።
7:4b.1CH.007.004ከእነርሱም ጋር በየትውልዳቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች ለሰልፍ የተዘጋጁ የሠራዊት ጭፍሮች ነበሩ፤ ብዙም ሴቶችና ልጆች ነበሩአቸውና ሠላሳ ስድስት ሺህ ነበሩ።
7:5b.1CH.007.005ወንድሞቻቸውም በይሳኮር ወገኖች ሁሉ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች በትውልዳቸው ሁሉ የተቈጠሩ ሰማኒያ ሰባት ሺህ ነበሩ።
7:6b.1CH.007.006የብንያም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ ይዲኤል ሦስት ነበሩ።
7:7b.1CH.007.007የቤላም ልጆች፥ ኤሴቦን፥ ኦዚ፥ ዑዝኤል፥ ኢያሪሙት፥ ዒሪ፥ አምስት ነበሩ፤ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ፤ በትውልድ የተቈጠሩ ሀያ ሁለት ሺህ ሠላሳ አራት ነበሩ።
7:8b.1CH.007.008የቤኬርም ልጆች፤ ዝሚራ፥ ኢዮአስ፥ አልዓዛር፥ ኤልዮዔናይ፥ ዖምሪ፥ ኢያሪሙት፥ አብያ፥ ዓናቶት፥ ዓሌሜት፤ እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ።
7:9b.1CH.007.009በየትውልዳቸው መዝገብ የተቈጠሩ፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ሀያ ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።
7:10b.1CH.007.010የይዲኤልም ልጅ ቢልሐን ነበረ፤ የቢልሐንም ልጆች የዑስ፥ ብንያም፥ ኤሁድ፥ ክንዓና፥ ዜታን፥ ተርሴስ፥ አኪሳአር ነበሩ።
7:11b.1CH.007.011እነዚህ ሁሉ የይዲኤል ልጆች ነበሩ፤ በየአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ጭፍራ እየሆኑ ወደ ሰልፍ የሚወጡ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች አሥራ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።
7:12b.1CH.007.012ደግሞም ሳፊን፥ ሑፊም የዒር ልጆች፥ ሑሺም የአሔር ልጆችም ነበሩ።
7:13b.1CH.007.013የንፍታሌም ልጆች፥ ያሕጽኤል፥ ጉኒ፥ ዬጽር፥ ሺሌም፥ የባላ ልጆች ነበሩ።
7:14b.1CH.007.014የምናሴ ልጆች ሶርያይቱ ቁባቱ የወለደችለት እሥርኤልና የገለዓድ አባት ማኪር ናቸው።
7:15b.1CH.007.015ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊን ወገን ሚስት አገባ፤ የእኅትዋም ስም መዓካ ነበረ፤ የሁለተኛውም ስም ሰለጰአድ ነበረ፤ ለሰለጰዓድም ሴቶች ልጆች ነበሩት።
7:16b.1CH.007.016የማኪርም ሚስት መዓካ ልጅ ወለደች፥ ስሙንም ፋሬስ ብላ ጠራችው፤ የወንድሙም ስም ሱሮስ ነበረ፤ ልጆቹም ኡላም፥ ራቄም ነበሩ።
7:17b.1CH.007.017የኡላምም ልጅ ባዳን ነበረ፤ እነዚህ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጆች ነበሩ።
7:18b.1CH.007.018እኅቱ መለኬት ኢሱድን፥ አቢዔዝርን፥ መሕላን ወለደች።
7:19b.1CH.007.019የሸሚዳም ልጆች አሒያን፥ ሴኬም፥ ሊቅሒ፥ አኒዓም ነበሩ።
7:20b.1CH.007.020የኤፍሬም ልጆች፤ ሹቱላ፥ ልጁ ባሬድ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ኤልዓዳ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ዛባድ፥ ልጁ ሽቱላ፥
7:21b.1CH.007.021የአገሩም ተወላጆች የጌት ሰዎች ከብቶቻቸውን ሊወስዱ ወርደው ነበርና የገደሉአቸው ልጆቹ ኤድርና ኤልዓድ ነበሩ።
7:22b.1CH.007.022አባታቸውም ኤፍሬም ብዙ ቀን አለቀሰ፥ ወንድሞቹም ሊያጽናኑት መጡ።
7:23b.1CH.007.023ወደ ሚስቱም ገባ፥ አረገዘችም፥ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤቱም መከራ ሆኖአልና ስሙ በሪዓ ብሎ ጠራው።
7:24b.1CH.007.024ሴት ልጁም ታችኛውንና ላይኛውን ቤትሖሮንንና ኡዜንሼራን የሠራች ሲአራ ነበረች።
7:25b.1CH.007.025ወንዶች ልጆቹም ፋፌ፥ ሬሴፍ፥ ልጁ ቴላ፥
7:26b.1CH.007.026ልጁ ታሐን፥ ልጁ ለአዳን፥ ልጁ ዓሚሁድ፥ ልጁ ኤሊሳማ፥
7:27b.1CH.007.027ልጁ ነዌ፥ ልጁ ኢያሱ።
7:28b.1CH.007.028ግዛታቸውና ማደሪያቸው ቤቴልና መንደሮችዋ፥ በምሥራቅም በኩል ነዓራን፥ በምዕራብም በኩል ጌዝርና መንደሮችዋ፥ ደግሞ ሴኬምና መንደሮችዋ እስከ ጋዛና እስከ መንደሮችዋ ድረስ፥
7:29b.1CH.007.029በምናሴም ልጆች ዳርቻ ቤትሳንና መንደሮችዋ፥ ታዕናክና መንደሮችዋ፥ መጊዶና መንደሮችዋ፥ ዶርና መንደሮችዋ ነበሩ፤ በእነዚህ የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ልጆች ተቀመጡ።
7:30b.1CH.007.030የአሴር ልጆች ዪምና፥ የሱዋ፥ የሱዊ፥ በሪዓ፥ እኅታቸውም ሤራሕ።
7:31b.1CH.007.031የበሪዓም ልጆች፤ ሔቤር፥ የቢርዛዊት አባት የነበረው መልኪኤል።
7:32b.1CH.007.032ሔቤርም ያፍሌጥን፥ ሳሜንር፥ ኮታምን፥ እኅታቸውንም ሶላን ወለደ።
7:33b.1CH.007.033የያፍሌጥም ልጆች ፋሴክ፥ ቢምሃል፥ ዓሲት ነበሩ፤ እነዚህ የያፍሌጥ ልጆች ነበሩ።
7:34b.1CH.007.034የሳሜርም ልጆች አኪ፥ ሮኦጋ፥ ይሑባ፥ አራም ነበሩ።
7:35b.1CH.007.035የወንድሙም የኤላም ልጆች ጾፋ፥ ይምና፥ ሰሌስ፥ ዓማል ነበሩ።
7:36b.1CH.007.036የጾፋም ልጆች ሱዋ፥ ሐርኔፍር፥
7:37b.1CH.007.037ሦጋል፥ ቤሪ፥ ይምራ፥ ቤጼር፥ ሆድ፥ ሳማ፥ ሰሊሳ፥ ይትራን፥ ብኤራ ነበሩ።
7:38b.1CH.007.038የዬቴር ልጆች ዮሮኒ፥ ፊስጳ፥ አራ ነበሩ።
7:39b.1CH.007.039የዑላ ልጆች ኤራ፥ ሐኒኤል፥ ሪጽያ ነበሩ።
7:40b.1CH.007.040እነዚህ ሁሉ የአሴር ልጆች፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ የተመረጡ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች፥ የመኳንንቱ አለቆች ነበሩ። በትውልዳቸውም በሰልፍ ለመዋጋት የተቈጠሩ ሀያ ስድስት ሺህ ሰዎች ነበሩ።
8
8:1b.1CH.008.001ብንያምም በኵሩን ቤላን፥ ሁለተኛውንም አስቤልን፥
8:2b.1CH.008.002ሦስተኛውንም አሐራን፥ አራተኛውንም ኖሐን፥ አምስተኛውንም ራፋን ወለደ።
8:3b.1CH.008.003ለቤላም ልጆች ነበሩት፤ አዳር፥
8:4b.1CH.008.004ጌራ፥ አቢሁድ፥ አቢሱ፥ ናዕማን፥ አሖዋ፥ ጌራ፥ ሰፉፋም፥ ሑራም።
8:5b.1CH.008.005እነዚህም የኤሁድ ልጆች ናቸው፤ እነዚህ በጌባ የሚቀመጡ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ናቸው፤
8:7b.1CH.008.007ወደ መናሐትም ተማረኩ፤ ናዕማን፥ አኪያ፥ ጌራ፥ እነርሱም ተማረኩ። ዖዛንና አሒሑድን ወለደ።
8:8b.1CH.008.008ሸሐራይምም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከሰደደ በኋላ በሞዓብ ሜዳ ልጆች ወለደ።
8:9b.1CH.008.009ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፥
8:10b.1CH.008.010ዲብያን፥ ማሴን፥ ማልካምን፥ ይዑጽን፥ ሻክያን፥ ሚርማን ወለደ። እነዚህም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆች ነበሩ።
8:11b.1CH.008.011ከሑሺምም አቢጡብንና ኤልፍዓልን ወለደ።
8:12b.1CH.008.012የኤልፍዓልም ልጆች፤ ዔቤር፥ ሚሻም፥ ኦኖንና ሎድን መንደሮቻቸውንም የሠራ ሻሚድ፤
8:13b.1CH.008.013በሪዓ፥ ሽማዕ የጌትን ሰዎች ያሳደዱ የኤሎን ሰዎች የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤
8:14b.1CH.008.014አሒዮ፥ ሻሻቅ፥ ይሬምት፥
8:15b.1CH.008.015ዝባድያ፥ ዓራድ፥ ዔድር፥ ሚካኤል፥ ይሽጳ፥ ዮሐ፥ የበሪዓ ልጆች፤
8:17b.1CH.008.017ዝባድያ፥ ሜሱላም፥
8:18b.1CH.008.018ሕዝቂ፥ ሔቤር፥ ይሽምራይ፥ ይዝሊያ፥ ዮባብ፥ የኤልፍዓል ልጆች፤
8:19b.1CH.008.019ያቂም፥ ዝክሪ፥ ዘብዲ፥
8:20b.1CH.008.020ኤሊዔናይ፥ ጺልታይ፥ ኤሊኤል፥ ዓዳያ፥ ብራያ፥ ሺምራት፥ የሰሜኢ ልጆች፤
8:22b.1CH.008.022ይሽጳን፥
8:23b.1CH.008.023ዔቤር፥ ኤሊኤል፥ ዓብዶን፥ ዝክሪ፥
8:24b.1CH.008.024ሐናን፥ ሐናንያ፥ ኤላም፥ ዓንቶትያ፥ ይፍዴያ፥ ፋኑኤል፥ የሶሴቅ ልጆች፤
8:26b.1CH.008.026ሸምሽራይ፥
8:27b.1CH.008.027ሸሃሪያ፥ ጎቶልያ፥ ያሬሽያ፥ ኤልያስ፥ ዝክሪ፥ የይሮሐም ልጆች።
8:28b.1CH.008.028እነዚህ በትውልዶቻቸው አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ፤ እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።
8:29b.1CH.008.029የሚስቱ ስም መዓካ የነበረው የገባዖን አባት ይዒኤል፥
8:30b.1CH.008.030የበኵር ልጁ ዓብዶን፥
8:31b.1CH.008.031ዱር፥ ቂስ፥ በኣል፥ ናዳብ፥ ጌዶር፥ አሒዮ፥ ዛኩር በገባዖን ተቀመጡ።
8:32b.1CH.008.032ሚቅሎት ሳምአን ወለደ፤ እነርሱ ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ተቀመጡ።
8:33b.1CH.008.033ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሚልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስባኣልን ወለደ።
8:34b.1CH.008.034የዮናታንም ልጅ መሪበኣል ነበረ፤ መሪበኣልም ሚካን ወለደ።
8:35b.1CH.008.035የሚካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ።
8:36b.1CH.008.036አካዝም ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዓሌሜትን፥ ዓዝሞትን፥ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ።
8:37b.1CH.008.037ሞጻም ቢንዓን ወለደ፤ ልጁም ረፋያ ነበረ፥ ልጁ ኤልዓሣ፥ ልጁ ኤሴል፤
8:38b.1CH.008.038ለኤሴልም ስድስት ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ዓዝሪቃም፥ ቦክሩ፥ እስማኤል፥ ሽዓርያ፥ አብድዩ፥ ሐናን፤ እነዚህ ሁሉ የኤሴል ልጆች ነበሩ።
8:39b.1CH.008.039የወንድሙም የአሴል ልጆች፤ በኵሩ ኡላም፥ ሁለተኛውም ኢያስ፥ ሦስተኛውም ኤሊፋላት።
8:40b.1CH.008.040የኡላም ልጆች ጽኑዓን ኃያላንና ቀስተኞች ነበሩ፤ ለእነርሱም መቶ አምሳ የሚያህሉ ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩአቸው፤ እነዚህ ሁሉ የብንያም ልጆች ነበሩ።
9
9:1b.1CH.009.001እስራኤልም ሁሉ በየትውልዳቸው ተቈጠሩ፤ እነሆም፥ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል። ይሁዳም ስለ ኃጢአታቸው ወደ ባቢሎን ተማረኩ።
9:2b.1CH.009.002በአውራጃዎቻቸውና በከተሞቻቸው መጀመሪያ የተቀመጡ እስራኤልና ካህናት ሌዋውያንም ናታኒምም ነበሩ።
9:3b.1CH.009.003ከይሁዳ ልጆችና ከብንያም ልጆች ከኤፍሬምና ከምናሴ ልጆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ።
9:4b.1CH.009.004ከይሁዳ ልጅ ከፋሬስ ልጆች የባኒ ልጅ የአምሪ ልጅ የፆምሪ ልጅ የዓሚሁድ ልጅ ዑታይ ደግሞ ተቀመጠ።
9:5b.1CH.009.005ከሴሎናዊያንም በኵሩ ዓሣያና ልጆቹ።
9:6b.1CH.009.006ከዛራም ልጆች ይዑኤልና ወንድሞቻቸው፥ ስድስት መቶ ዘጠና።
9:7b.1CH.009.007ከብንያምም ልጆች የሐስኑአ ልጅ የሆዳይዋ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሉ፤
9:8b.1CH.009.008የይሮሐም ልጅ ብኔያ፤ የሚክሪ ልጅ የኦዚ ልጅ ኤላ፤ የዪብኒያ ልጅ የራጉኤል ልጅ የሰፋጥያስ ልጅ ሜሱላም፤
9:9b.1CH.009.009በየትውልዳቸውም ወንድሞቻቸው ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስድስት ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ።
9:10b.1CH.009.010ከካህናቱም ዮዳሄ፥ ዮአሪብ፥ ያኪን፤
9:11b.1CH.009.011የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ የመራዮት ልጅ የሳዶቅ ልጅ ሜሱላም ልጅ የኬልቂያስ ልጅ ዓዛርያስ፤
9:12b.1CH.009.012የመልኪያ ልጅ የጳስኮር ልጅ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፤ የኢሜር ልጅ የምሺላሚት ልጅ የሜሱላም ልጅ የየሕዜራ ልጅ የዓዲኤል ልጅ መዕሣይ፤
9:13b.1CH.009.013የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች ወንድሞቻቸው ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ነበሩ፤ ለእግዚአብሔር ቤት ማገልገል ሥራ እጅግ ብልሃተኞች ሰዎች ነበሩ።
9:14b.1CH.009.014ከሌዋውያንም የሜራሪ ልጆች የአሳብያ ልጅ የዓዝሪቃም ልጅ የአሱብ ልጅ ሸማያ፤
9:15b.1CH.009.015በቅበቃር፥ ኤሬስ፥ ጋላል፥ የኣሳፍ ልጅ የዝክሪ ልጅ የሚካ ልጅ መታንያ፤
9:16b.1CH.009.016የኤዶታም ልጅ የጋላል ልጅ የሰሙስ ልጅ አብድያ፤ በነጦፋውያንም መንደሮች የተቀመጠው የሕልቃና ልጅ የአሳ ልጅ በራክያ።
9:17b.1CH.009.017በረኞችም ሰሎም፥ ዓቁብ፥ ጤልሞን፥ አሒማን፥ ወንድሞቻቸውም ነበሩ፤ ሰሎምም አለቃ ነበረ።
9:18b.1CH.009.018እስከ ዛሬም ድረስ በንጉሥ በር በምሥራቅ በኩል ነበሩ፤ ለሌዊ ልጆች ሰፈር በረኞች ነበሩ።
9:19b.1CH.009.019የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱም ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፥ የድንኳኑንም መድረክ ይጠብቁ ነበር። አባቶቻቸውም የእግዚአብሔርን ሰፈር መግቢያ ጠብቀው ነበር።
9:20b.1CH.009.020አስቀድሞም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ አለቃቸው ነበረ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ።
9:21b.1CH.009.021የሜሱላም ልጅ ዘካርያስ የመገናኛው ድንኳን ደጅ በረኛ ነበረ።
9:22b.1CH.009.022የመድረኩ በረኞች ይሆኑ ዘንድ የተመረጡ እነዚህ ሁሉ ሁለት መቶ አሥራ ሁለት ነበሩ። ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል በሥራቸው ያቆሙአቸው እነዚህ በመንደሮቻቸው በየትውልዳቸው ተቈጠሩ።
9:23b.1CH.009.023እነርሱና ልጆቻቸውም በእግዚአብሔር ቤት በድንኳኑ ደጆች ላይ ዘበኞች ነበሩ።
9:24b.1CH.009.024በአራቱ ማዕዘኖች፥ በምሥራቅ፥ በምዕራብ፥ በሰሜን፥ በደቡብ፥ በረኞች ነበሩ።
9:25b.1CH.009.025ወንድሞቻቸውም በመንደሮቻቸው ሆነው፥ በየሰባትም ቀን ከእነርሱ ጋር ሊሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይገቡ ነበር።
9:26b.1CH.009.026ከሌዋውያንም የነበሩ አራቱ የበረኞች አለቆች ዘወትር በሥራቸው ይቀመጡ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ቤት ባሉ ጓዳዎችና ቤተ መዛግብት ላይ ነበሩ።
9:27b.1CH.009.027የእግዚአብሔርንም ቤት የሚጠብቁ፥ ጥዋት ጥዋትም ደጆቹን የሚከፍቱ እነርሱ ነበሩና በዚያ ያድሩ ነበር።
9:28b.1CH.009.028ዕቃውም በቍጥር ይገባና ይወጣ ነበርና ከእነዚህ አንዳንዱ በማገልገያው ዕቃ ላይ ሹሞች ነበሩ።
9:29b.1CH.009.029ከእነርሱም አንዳንዶቹ በመቅደሱ ዕቃ ሁሉ በመልካሙም ዱቄት፥ በወይን ጠጁ፥ በዘይቱም፥ በዕጣኑም፥ በሽቱውም ላይ ሹሞች ነበሩ።
9:30b.1CH.009.030ከካህናቱም ልጆች አንዳንዶቹ የሽቱውን ቅባት ያጣፍጡ ነበር።
9:31b.1CH.009.031የቆሬያዊውም የሰሎም በኵር ሌዋዊው ማቲትያ በምጣድ በሚጋገረው ነገር ላይ ሹም ነበረ።
9:32b.1CH.009.032በየሰንበቱም ያዘጋጁ ዘንድ ከወንድሞቻቸው ከቀዓታውያን አንዳንዱ በገጹ ኅብስት ላይ ሹሞች ነበሩ።
9:33b.1CH.009.033ከሌዋውያኑም ወገን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች የነበሩ መዘምራን እነዚህ ናቸው፤ ሥራቸውም ሌሊትና ቀን ነበረና ያለሌላ ሥራ በየጓዳቸው ይቀመጡ ነበር።
9:34b.1CH.009.034እነዚህ ከሌዋውያን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች በየትውልዳቸው አለቆች ነበሩ። እነዚህም በኢየሩሳሌም ይቀመጡ ነበር።
9:35b.1CH.009.035የሚስቱ ስም መዓካ የነበረው የገባዖን አባት ይዒኤል፥
9:36b.1CH.009.036የበኵር ልጁም ዓብዶን፥
9:37b.1CH.009.037ዱር፥ ቂስ፥ በኣል፥ ኔር፥ ናዳብ፥ ጌዶር፥ አሒዮ፥ ዛኩር፥ ሚቅሎት፥ በገባኦን ይቀመጡ ነበር።
9:38b.1CH.009.038ሚቅሎትም ሳምአን ወለደ፤ እነርሱ ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ይቀመጡ ነበር።
9:39b.1CH.009.039ኔርም ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሚልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስበኣልን ወለደ።
9:40b.1CH.009.040የዮናታንም ልጅ መሪበኣል ነበረ፤ መሪበኣልም ሚካን ወለደ።
9:41b.1CH.009.041የሚካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታሬዓ፥ አካዝ ነበሩ።
9:42b.1CH.009.042አካዝም የዕራን ወለደ፤ የዕራም ዓሌሜትን፥ ዓዝሞትን፥ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ።
9:43b.1CH.009.043ሞጻም ቢንዓን ወለደ፥ ልጁም ረፋያ ነበረ፥ ልጁ ኤልዓሣ፥ ልጁ ኤሴል፤
9:44b.1CH.009.044ለኤሴልም ስድስት ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ዓዝሪቃም፥ ቦክሩ፥ እስማኤል፥ ሸዓሪያ፥ አብድዩ፥ ሐናን፤ እነዚህ የኤሴል ልጆች ነበሩ።
10
10:1b.1CH.010.001ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ተዋጉ፤ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፥ ተወግተውም በጊልቦአ ተራራ ላይ ወደቁ።
10:2b.1CH.010.002ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን በእግር በእግራቸው ተከትለው አባረሩአቸው፤ ፍልስጥኤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንንና አሚናዳብን ሜልኪሳንም ገደሉ።
10:3b.1CH.010.003ሰልፍም በሳኦል ላይ ጠነከረ፥ ቀስተኞችም አገኙት፤ ከቀስተኞችም የተነሣ ተጨነቀ።
10:4b.1CH.010.004ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን። እነዚህ ቈላፋን መጥተው እንዳይዘብቱብኝ ሰይፍህን መዝዘህ ውጋኝ አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ነበርና እንቢ አለ። ሳኦልም ሰይፉን ወስዶ በላዩ ወደቀ።
10:5b.1CH.010.005ጋሻ ጃግሬውም ሳኦል እንደ ሞተ ባየ ጊዜ እርሱ ደግሞ በሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።
10:6b.1CH.010.006ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ የቤቱም ሰዎች ሁሉ በአንድ ላይ ሞቱ።
10:7b.1CH.010.007በሸለቆውም የነበሩት የእስራኤል ሰዎች ሁሉ እንደ ሸሹ፥ ሳኦልና ልጆቹም እንደ ሞቱ ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ለቅቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።
10:8b.1CH.010.008በነጋውም ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልንና ልጆቹን በጊልቦአ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው።
10:9b.1CH.010.009ገፈፉትም፥ ራሱንና መሣሪያውንም አንሥተው ለጣኦቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራች ይወስዱ ዘንድ ወደ ፍልስጥኤማውያን አገር ዙሪያ ሰደዱ።
10:10b.1CH.010.010መሣሪያውንም በአምላኮቻቸው ቤት ውስጥ አኖሩ፤ ራሱንም በዳጎን ቤት ውስጥ ቸነከሩት።
10:11b.1CH.010.011የኢያቢስ ገለዓድም ሰዎች ሁሉ ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን ሁሉ በሰሙ ጊዜ፥
10:12b.1CH.010.012ጽኑአን ሰዎች ሁሉ ተነሥተው የሳኦልን ሬሳ የልጆቹንም ሬሳ ወሰዱ፥ ወደ ኢያቢስም አመጡአቸው፤ በኢያቢስም ካለው ከትልቁ ዛፍ በታች አጥንቶቻቸውን ቀበሩ፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።
10:13b.1CH.010.013እንዲሁ ሳኦል በእግዚአብሔር ላይ ስላደረገው ኃጢአት፥ የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪ
10:14b.1CH.010.014ስለ ጠየቀ እግዚአብሔርንም ስላልጠየቀ፥ ስለዚህ ገደለው፥ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አሳለፈው።
11
11:1b.1CH.011.001እስራኤልም ሁሉ በኬብሮን ወደ ዳዊት ተሰብስበው። እነሆ፥ እኛ የአጥንትህ ፍላጭ የሥጋህ ቍራጭ ነን፤
11:2b.1CH.011.002አስቀድሞ ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን የምታወጣና የምታገባ አንተ ነበርህ፤ አምላክህ እግዚአብሔርም። ሕዝቤን እስራኤልን አንተ ትጠብቃለህ፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆናለህ 5ብሎህ ነበር አሉት።
11:3b.1CH.011.003የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትም በኬብሮን በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደረገ፤ በሳሙኤልም እጅ እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል በእስራኤል ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊትን ቀቡት።
11:4b.1CH.011.004ዳዊትም እስራኤልም ሁሉ ኢያቡስ ወደምትባል ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፤ በአገሩም የተቀመጡ ኢያቡሳውያን በዚያ ነበሩ።
11:5b.1CH.011.005በኢያቡስም የተቀመጡ ዳዊትን። ወደዚህ አትገባም አሉት፤ ዳዊት ግን አምባይቱን ጽዮንን ያዘ፤ እርሷም የዳዊት ከተማ ናት።
11:6b.1CH.011.006ዳዊትም። ኢያቡሳውያንን አስቀድሞ የሚመታ ሰው አለቃና መኰንን ይሆናል አለ። የጽሩያም ልጅ ኢዮአብ አስቀድሞ ወጣ፥ አለቃም ሆነ።
11:7b.1CH.011.007ዳዊትም በአምባይቱ ውስጥ ተቀመጠ፤ ስለዚህም የዳዊት ከተማ ብለው ጠሩአት።
11:8b.1CH.011.008ከሚሎም ጀምሮ በዙሪያው ከተማ ሠራ፤ ኢዮአብም የቀረውን ከተማ አበጀ።
11:9b.1CH.011.009ዳዊትም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና እየበረታ ሄደ።
11:10b.1CH.011.010ለዳዊትም የነበሩት የኃያላን አለቆች እነዚህ ናቸው፤ ስለ እስራኤል እንደ ተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ያነግሡት ዘንድ ከእስራኤል ሁሉ ጋር በመንግሥቱ ላይ አጸኑት።
11:11b.1CH.011.011የዳዊትም ኃያላን ቍጥር ይህ ነበረ፤ የሠላሳው አለቃ የአክሞናዊው ልጅ ያሾብአም ነበረ፤ እርሱ ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰው በአንድ ጊዜ ገደለ።
11:12b.1CH.011.012ከእርሱም በኋላ በሦስቱ ኃያላን መካከል የነበረ የአሆሃሂው የዱዲ ልጅ አልዓዛር ነበር።
11:13b.1CH.011.013እርሱ ከዳዊት ጋር በፈስደሚም ነበረ፥ በዚያም ገብስ በሞላበት እርሻ ውስጥ ፍልስጥኤማውያን ለሰልፍ ተሰብስበው ነበር፤ ሕዝቡም ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ።
11:14b.1CH.011.014በእርሻውም መካከል ቆመው ጠበቁት፥ ፍልስጥኤማውያንንም ገደሉ፤ እግዚአብሔርም በታላቅ ማዳን አዳናቸው።
11:15b.1CH.011.015ከሠላሳውም አለቆች ሦስቱ ወርደው ዳዊት ወዳለበት ወደ ዓለቱ ወደ ዓዶላም ዋሻ መጡ፤ የፍልስጥኤማውያንም ጭፍራ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።
11:16b.1CH.011.016በዚያም ጊዜ ዳዊት በምሽጉ ውስጥ ነበረ፥ የፍልስጥኤማውያንም ጭፍራ በቤተ ልሔም ነበረ።
11:17b.1CH.011.017ዳዊትም። በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውሃ ማን ይሰጠኛል? ብሎ ተመኘ።
11:18b.1CH.011.018እነዚህም ሦስቱ የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ቀድደው ሄዱ፥ በበሩም አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውሃ ቀዱ፤ ይዘውም ለዳዊት አመጡለት። እርሱ ግን ሊጠጣ አልወደደም፥ ነገር ግን ለእግዚአብሔር አፍስሶ።
11:19b.1CH.011.019ይህን አደርግ ዘንድ አምላኬ ይከልክለኝ፤ በነፍሳቸው የደፈሩትም እነዚህ ሰዎች ደም እጠጣለሁን? በነፍሳቸው አምጥተውታል አለ። ስለዚህም ይጠጣ ዘንድ አልወደደም። ሦስቱም ኃያላን ያደረጉት ይህ ነው።
11:20b.1CH.011.020የኢዮአብም ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ፤ ጦሩንም በሦስት መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፥ በሦስቱም መካከል ስሙ የተጠራ ነበረ።
11:21b.1CH.011.021በሁለተኛውም ተራ በሆኑት በሦስቱ መካከል የከበረ ነበረ፥ አለቃቸውም ሆነ፤ ነገር ግን ወደ ፊተኞቹ ወደ ሦስቱ አልደረሰም።
11:22b.1CH.011.022በቀብስኤልም የነበረው፥ ታላቅ ሥራ ያደረገው የጽኑዕ ሰው የዮዳሄ ልጅ በናያስ የሞዓባዊን የአሪኤል ሁለቱን ልጆች ገደለ፤ በአመዳይም ወራት ወርዶ በጕድጓድ ውስጥ አንበሳ ገደለ።
11:23b.1CH.011.023ቁመቱም አምስት ክንድ የነበረውን ረጅሙን ግብጻዊውን ሰው ገደለ፤ በግብጻዊውም እጅ የሸማኔ መጠቅለያ የመሰለ ጦር ነበረ፤ እርሱ ግን በትር ይዞ ወደ እርሱ ወረደ፥ ከግብጻዊውም እጅ ጦሩን ነቅሎ በገዛ ጦሩ ገደለው።
11:24b.1CH.011.024የዮዳሄ ልጅ በናያስ ያደረገው ይህ ነው፤ ስሙም በሦስቱ ኃያላን መካከል የተጠራ ነበር።
11:25b.1CH.011.025እነሆ፥ ከሠላሳው ይልቅ የከበረ ነበረ፥ ነገር ግን ወደ ፊተኞቹ ወደ ሦስቱ አልደረሰም። ዳዊትም በዘበኞቹ ላይ ሾመው።
11:26b.1CH.011.026ደግሞም በጭፍሮች ዘንድ የነበሩት ኃያላን እነዚህ ናቸው፤ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፥
11:27b.1CH.011.027ሃሮራዊው ሳሞት፥ ፈሎናዊው ሴሌስ፥
11:28b.1CH.011.028የቴቁሔ ሰው የዒስካ ልጅ ዒራስ፥
11:29b.1CH.011.029ዓናቶታዊው አቢዔዜር፥ ኩሳታዊው ሴቤካይ፥
11:30b.1CH.011.030አሆሃዊው ዔላይ፥ ነጦፋዊው ኖኤሬ፥ የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌድ፥
11:31b.1CH.011.031ከብንያም ወገን ከግብዓ የሪባይ ልጅ ኤታይ፥
11:32b.1CH.011.032ጲርዓቶናዊው በናያስ፥ የገዓስ ወንዝ ሰው ኡሪ፥
11:33b.1CH.011.033ዓረባዊው አቢኤል፥ ባሕሩማዊው ዓዝሞት፥
11:34b.1CH.011.034ሰዓልቦናዊው ኤሊያሕባ፥ የጊዞናዊው የአሳን ልጆች፥ የሃራራዊው የሻጌ ልጅ ዮናታን፥
11:35b.1CH.011.035የአሮዳዊው የአራር ልጅ አምናን፥
11:36b.1CH.011.036የኡር ልጅ ኤሊፋል፥ ሚኬራታዊው ኦፌር፥
11:37b.1CH.011.037ፍሎናዊው አኪያ፥ ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ፥ የኤዝባይ ልጅ ነዕራይ፥
11:38b.1CH.011.038የናታንም ወንድም ኢዮኤል፥ የሐግሪ ልጅ ሚብሐር፥
11:39b.1CH.011.039አሞናዊው ጼሌቅ፥ የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬ ቤሮታዊው ነሃራይ፥
11:40b.1CH.011.040ይትራዊው ዒራስ፥ ይትራዊው ጋሬብ፥
11:41b.1CH.011.041ኬጢያዊው ኦርዮ፥ የአሕላይ ልጅ ዛባድ፥
11:42b.1CH.011.042የሮቤላዊው የሺዛ ልጅ ዓዲና፥ እርሱ የሮቤላውያን አለቃ ነበረ፥
11:43b.1CH.011.043ከእርሱም ጋር ሠላሳ ሰዎች ነበሩ፥ የማዕካ ልጅ ሐናን፥ ሚትናዊው ኢዮሣፍጥ፥
11:44b.1CH.011.044አስታሮታዊው ዖዝያ፥ የአሮኤራዊው የኮታም ልጆች ሻማና ይዒኤል፥
11:45b.1CH.011.045የሽምሪ ልጅ ይድኤል፥ ወንድሙም ይድኤል፥ ወንድሙም ቲዳዊው ዮሐ፥
11:46b.1CH.011.046መሐዋዊው ኤሊኤል፥ ይሪባይ፥ ዮሻዊያ፥ የኤልናዓም ልጆች፥ ሞዓባዊው ይትማ፥
11:47b.1CH.011.047ኤልኤል፥ ዖቤድ፥ ምጾባዊው የዕሢኤል።
12
12:1b.1CH.012.001በጺቅላግም ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት የመጡ እነዚህ ናቸው፤ በሰልፍም ባገዙት ኃያላን መካከል ነበሩ።
12:2b.1CH.012.002ቀስተኞችም ነበሩ፥ በቀኝና በግራም እጃቸው ድንጋይ ሊወነጭፉ ፍላጻም ሊወረውሩ ይችሉ ነበር፤ ከብንያም ወገን የሳኦል ወንድሞች ነበሩ።
12:3b.1CH.012.003አለቃቸው አሒዔዝር ነበረ፥ ከእርሱም በኋላ ኢዮአስ፥ የጊብዓዊው የሸማዓ ልጆች፤ ይዝኤል፥ ፋሌጥ፥ የዓዝሞት ልጆች፤ በራኪያ፥ ዓናቶታዊው ኢዩ፥
12:4b.1CH.012.004ገባዖናዊው ሰማያስ፥ እርሱ በሠላሳው መካከልና በሠላሳው ላይ ኃያል ሰው ነበረ፤ ኤርምያስ፥ የሕዚኤል፥ ዮሐናን፥
12:5b.1CH.012.005ገድሮታዊው ዮዛባት፥ ኤሉዛይ፥ ኢያሪሙት፥ በዓልያ፥ ሰማራያ፥ ሀሩፋዊው ሰፋጥያስ፥
12:6b.1CH.012.006ቆርያውያን ሕልቃና፥ ይሺያ፥ አዛርኤል፥ ዮዛር፥ ያሾቢአም፤
12:7b.1CH.012.007የጌዶር ሰው የይሮሃም ልጆች የኤላ፥ ዝባድያ
12:8b.1CH.012.008ዳዊትም ከምድረ በዳ ውስጥ ባለችው በአንባይቱ ሳለ ከጋድ ወገን የሆኑ እነዚህ ጋሻና ጦር የሚይዙ፥ ጽኑዓን ኃያላን፥ ሰልፈኞች፥ ወደ እርሱ ተጠጉ፤ ፊታቸውም እንደ አንበሳ ፊት ነበረ፥ በተራራም ላይ እንደሚዘልል ሚዳቋ ፈጣኖች ነበሩ።
12:9b.1CH.012.009አለቃው ዔጼር፥ ሁለተኛው አብድዩ፥
12:10b.1CH.012.010ሦስተኛው ኤልያብ፥ አራተኛው መስመና፥
12:11b.1CH.012.011አምስተኛው ኤርምያስ፥ ስድስተኛው አታይ፥
12:12b.1CH.012.012ሰባተኛው ኤሊኤል፥ ስምንተኛው ዮሐናን፥
12:13b.1CH.012.013ዘጠነኛው ኤልዛባድ፥ አሥረኛው ኤርምያስ፥ አሥራ አንደኛው መክበናይ።
12:14b.1CH.012.014እነዚህ የጋድ ልጆች የጭፍራ አለቆች ነበሩ፤ ከእነርሱም ታናሹ ከመቶ፥ ታላቁ ከሺህ ይመዛዘኑ ነበር።
12:15b.1CH.012.015በመጀመሪያው ወር ዮርዳኖስ ከዳር እስከ ዳር ሞልቶ በነበረ ጊዜ የተሻገሩት እነዚህ ናቸው፤ በሸለቆውም ውስጥ በምሥራቅና በምዕራብ በኩል የተቀመጡትን ሁሉ አባረሩ።
12:16b.1CH.012.016ዳዊትም ወደነበረባት ወደ አምባይቱ ከብንያምና ከይሁዳ ወገን ሰዎች መጡ።
12:17b.1CH.012.017ዳዊትም ሊገናኛቸው ወጥቶ። ትረዱኝ ዘንድ በሠላም ወደ እኔ መጥታችሁ እንደ ሆነ ልቤ ከእናንተ ጋር አንድ ይሆናል፤ ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ መጥታችሁ እንደሆነ ግን፥ በእጄ ዓመፅ የለብኝምና የአባቶቻችን አምላክ ይመልከተው፥ ይፍረደውም አላቸው።
12:18b.1CH.012.018መንፈስም በሠላሳው አለቃ በአማሳይ ላይ መጣ፥ እርሱም። ዳዊት ሆይ፥ እኛ የአንተ ነን፤ የእሴል ልጅ ሆይ፥ እኛ ከአንተ ጋር ነን፤ አምላክህ ይረዳሃልና ሰላም ሰላም ለአንተ ይሁን፥ ለሚረዱህም ሰላም ይሁን አለ። ዳዊትም ተቀበላቸው፥ የጭፍራም አለቆች አደረጋቸው።
12:19b.1CH.012.019ዳዊትም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሳኦልን ሊወጋ በመጣ ጊዜ ከምናሴ ወገን ሰዎች ወደ ዳዊት ከዱ፤ የፍልስጥኤማውያን አለቆች ግን። በራሳችን ላይ ጕዳት አድርጎ ወደ ጌታው ወደ ሳኦል ይመለሳል ሲሉ ተማክረው ሰድደውታልና እነርሱ አልረዷቸውም።
12:20b.1CH.012.020ወደ ጺቅላግም ሲሄድ ከምናሴ ወገን የምናሴ ሻለቆች የነበሩ ዓድና፥ ዮዛባት፥ ይዲኤል፥ ሚካኤል፥ ዮዛባት፥ ኤሊሁ፥ ጺልታይ ወደ እርሱ ከዱ።
12:21b.1CH.012.021ሁሉም ጽኑዓን ኃያላንና በሠራዊቱ ላይ አለቆች ነበሩና በአደጋ ጣዮቹ ላይ ዳዊትን አገዙት።
12:22b.1CH.012.022እንደ እግዚአብሔርም ሠራዊት ታላቅ ሠራዊት እስኪሆን ድረስ ዳዊትን ለመርዳት ዕለት ዕለት ይመጡ ነበር።
12:23b.1CH.012.023እንደ እግዚአብሔርም ቃል የሳኦልን መንግሥት ወደ እርሱ ይመልሱ ዘንድ በኬብሮን ሳለ ወደ ዳዊት የመጡት የሠራዊቱ አለቆች ቍጥር ይህ ነው።
12:24b.1CH.012.024ጋሻና ጦር ተሸክመው ለሰልፍ የተዘጋጁ የይሁዳ ልጆች ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ነበሩ።
12:25b.1CH.012.025ለሰልፍ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች የነበሩ የስምዖን ልጆች ሰባት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ።
12:26b.1CH.012.026የሌዊ ልጆች አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።
12:27b.1CH.012.027የአሮንም ቤት አለቃ ዮዳሄ ነበረ፥ ከእርሱም ጋር ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ፤
12:28b.1CH.012.028ከእርሱም ጋር ጽኑዕ ኃያል ጕልማሳ ሳዶቅ ነበረ፥ ከአባቱም ቤት ሃያ ሁለት አለቆች ነበሩ።
12:29b.1CH.012.029የሳኦልም ወንድሞች ከሆኑ ከብንያም ወንድሞች የሚበልጠው ክፍል እስከዚያ ዘመን ድረስ የሳኦልን ቤት ይከተል ነበርና ከእነርሱ ዘንድ የመጡ ሦስት ሺህ ነበሩ።
12:30b.1CH.012.030ጽኑዓን ኃያላን የሆኑ በአባቶቻቸውም ቤት የታወቁ የኤፍሬም ልጆች ሀያ ሺህ ስምንት መቶ ነበሩ።
12:31b.1CH.012.031በየስማቸውም የተጻፉ ዳዊትን ያነግሡት ዘንድ የመጡ የምናሴ ነገድ እኵሌታ አሥራ ስምንት ሺህ ነበሩ።
12:32b.1CH.012.032እስራኤልም የሚገባውን ያደርግ ዘንድ ዘመኑን የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ይታዘዙአቸው ነበር።
12:33b.1CH.012.033በጭፍራውም ውስጥ የወጡ ለሰልፍም የተዘጋጁ፥ የማያመነቱ፥ መሣሪያም ሁሉ የያዙ የዛብሎን ሰዎች አምሳ ሺህ ነበሩ።
12:34b.1CH.012.034የንፍታሌምም አለቆች አንድ ሺህ ነበሩ፥ ከእነርሱም ጋር ጋሻና ጦር የሚይዙ ሠላሳ ሰባት ሺህ ነበሩ።
12:35b.1CH.012.035ለሰልፍም የተዘጋጁ የዳን ሰዎች ሃያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።
12:36b.1CH.012.036በጭፍራውም ውስጥ የሚወጡ፥ ለሰልፍም የተዘጋጁ የአሴር ሰዎች አርባ ሺህ ነበሩ።
12:37b.1CH.012.037በዮርዳኖስም ማዶ ካሉ ከሮቤልና ከጋድ ሰዎች ከምናሴም ነገድ እኵሌታ መሣሪያን ሁሉ ይዘው የመጡ መቶ ሀያ ሺህ ነበሩ።
12:38b.1CH.012.038እነዚህ ሁሉ ዳዊትን በእስራኤል ሁሉ ላይ ያነግሡት ዘንድ አርበኞችና ሰልፈኞች እየሆኑ በፍጹም ልባቸው ወደ ኬብሮን መጡ፤ ደግሞም ከእስራኤል የቀሩት ሁሉ ዳዊትን ያነግሡት ዘንድ አንድ ልብ ነበሩ።
12:39b.1CH.012.039ወንድሞቻቸውም አዘጋጅተውላቸው ነበርና እየበሉና እየጠጡ በዚያ ከዳዊት ጋር ሦስት ቀን ተቀመጡ።
12:40b.1CH.012.040ደግሞም በእስራኤል ዘንድ ደስታ ሆኖአልና እስከ ይሳኮርና እስከ ዛብሎን እስከ ንፍታሌምም ድረስ ለእርሱ አቅራቢያ የነበሩ በአህያና በግመል በበቅሎና በበሬ ላይ እንጀራና ዱቄት የበለስ ጥፍጥፍና የዘቢበ ዘለላ የወይንም ጠጅ ዘይትም በሬዎችንና በጎችንም በብዙ አድርገው ያመጡ ነበር።
13
13:1b.1CH.013.001ዳዊትም ከሻለቆችና ከመቶ አለቆች ከአለቆቹም ሁሉ ጋር ተማከረ።
13:2b.1CH.013.002ዳዊትም የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ። መልካም መስሎ የታያችሁ እንደሆነ፥ ከአምላካችን ከእግዚአብሔርም ወጥቶ እንደ ሆነ፥ በእስራኤል አገር ሁሉ ለቀሩት ወንድሞቻችን በከተሞቻቸውና በመሰምሪያዎቻቸውም ለሚቀመጡ ካህናትና ሌዋውያን ወደ እኛ ይሰበሰቡ ዘንድ እንላክ፤
13:3b.1CH.013.003በሳኦልም ዘመን አልፈለግነውምና የአምላካችንን ታቦት ወደ እኛ እንመልስ አላቸው።
13:4b.1CH.013.004ነገሩም በሕዝቡ ሁሉ ዓይን ዘንድ ቅን ነበረና ጉባኤው ሁሉ። እንዲሁ እናደርጋለን አሉ።
13:5b.1CH.013.005የእግዚአብሔርንም ታቦት ከቂርያትይዓሪም ያመጡ ዘንድ ዳዊት እስራኤልን ሁሉ ከግብጽ ወንዝ ከሺሖር ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ ሰበሰበ።
13:6b.1CH.013.006ዳዊትም እስራኤልም ሁሉ በኪሩቤል ላይ የተቀመጠውን ስሙም በእርሱ የተጠራውን የአምላክን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ያወጡ ዘንድ በይሁዳ ወዳለችው ቂርያትይዓሪም ወደ ተባለች ወደ በኣላ ሄዱ።
13:7b.1CH.013.007የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሰረገላ ላይ ጫኑት፥ ከአሚናዳብም ቤት አመጡት፤ ዖዛና አሒዮም ሠረገላውን ይነዱ ነበር።
13:8b.1CH.013.008ዳዊትና እስራኤል ሁሉ በቅኔና በበገና በመሰንቆና በከበሮ በጸናጽልና በመለከት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይላቸው ይጫወቱ ነበር።
13:9b.1CH.013.009ወደ ኪዶንም አውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ ይፋንኑ ነበርና ታቦቱን ሊይዝ ዖዛ እጁን ዘረጋ።
13:10b.1CH.013.010የእግዚአብሔርም ቍጣ በዖዛ ላይ ነደደ፥ እጁንም ወደ ታቦቱ ስለ ዘረጋ ቀሠፈው፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ሞተ።
13:11b.1CH.013.011እግዚአብሔርም ዖዛን ስለ ቀሠፈው ዳዊት አዘነ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የዚያን ስፍራ ስም የዖዛ ስብራት ብሎ ጠራው።
13:12b.1CH.013.012በዚያም ቀን ዳዊት። የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኔ እንዴት አመጣለሁ ብሎ እግዚአብሔርን ፈራ።
13:13b.1CH.013.013ዳዊትም ታቦቱን ወደ ጌት ሰው ወደ አቢዳራ ቤት አሳለፈው እንጂ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ አላመጣውም።
13:14b.1CH.013.014የእግዚአብሔርም ታቦት በአቢዳራ ቤተሰብ ዘንድ በቤቱ ውስጥ ሦስት ወር ተቀመጠ፤ እግዚአብሔርም የአቢዳራን ቤትና ያለውን ሁሉ ባረከ።
14
14:1b.1CH.014.001የጢሮስም ንጉሥ ኪራም ቤት ይሠሩለት ዘንድ መልእክተኞችን የዝግባ እንጨትንም ጠራቢዎችንም አናጢዎችንም ወደ ዳዊት ላከ።
14:2b.1CH.014.002ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል መንግሥቱ ከፍ ብሎአልና እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናው ዳዊት አወቀ።
14:3b.1CH.014.003ዳዊትም በኢየሩሳሌም ሚስቶችን ጨምሮ ሌሎችን ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ወለደ።
14:4b.1CH.014.004በኢየሩሳሌምም የወለዳቸው የልጆቹ ስም ይህ ነው፤ ሳሙስ፥
14:5b.1CH.014.005ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎሞን፥ ኢያቤሐር፥ ኤሊሱዔ፥
14:6b.1CH.014.006ኤሊፋላት፥ ኖጋ፥ ናፌቅ፥ ያፍያ፥
14:7b.1CH.014.007ኤሊሳማ፥ ኤሊዳሄ፥ ኤሊፋላት።
14:8b.1CH.014.008ፍልስጥኤማውያንም ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደተቀባ ሰሙ፥ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ዳዊትን ሊፈልጉ ወጡ፤ ዳዊትም በሰማ ጊዜ ሊጋጠማቸው ወጣ።
14:9b.1CH.014.009ፍልስጥኤማውያንም መጥተው በራፋይም ሸለቆ አደጋ ጣሉ።
14:10b.1CH.014.010ዳዊትም። ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም። በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ አለው።
14:11b.1CH.014.011ወደ በአልፐራሲም ወጡ፥ በዚያም ዳዊት መታቸው። ዳዊትም። ውኃ እንዲያፈርስ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በእጄ አፈረሳቸው አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በአልፐራሲም ብለው ጠሩት።
14:12b.1CH.014.012አማልክቶቻቸውንም በዚያ ተዉ፤ ዳዊትም አዘዘ፥ በእሳትም አቃጠሏቸው።
14:13b.1CH.014.013ፍልስጥኤማውያንም ደግሞ በሸለቆው አደጋ ጣሉ።
14:14b.1CH.014.014ዳዊትም እንደ ገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም። ከእነርሱ ዞረህ በሾላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠማቸው እንጂ ወደ እነርሱ አትውጣ።
14:15b.1CH.014.015በሾላውም ዛፍ እራስ ውስጥ የሽውሽውታ ድምፅ ስትሰማ የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ ሊመታ እግዚአብሔር በፊትህ ይወጣልና በዚያን ጊዜ ወደ ሰልፍ ውጣ አለው።
14:16b.1CH.014.016ዳዊትም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ከገባዖንም ጀምሮ እስከ ጌዝር ድረስ የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ መቱት።
14:17b.1CH.014.017የዳዊትም ዝና በየአገሩ ሁሉ ወጣ፤ መፈራቱንም እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ አደረገው።
15
15:1b.1CH.015.001ዳዊትም በከተማው ላይ ለራሱ ቤቶችን ሠራ፤ ለእግዚአብሔርም ታቦት ስፍራ አዘጋጀ፥ ድንኳንም ተከለለት።
15:2b.1CH.015.002በዚያን ጊዜም ዳዊት። የእግዚአብሔርን ታቦት ይሸከሙ ዘንድ፥ ለዘላለሙም ያገለግሉት ዘንድ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር ማንም የእግዚአብሔርን ታቦት ይሸከም ዘንድ አይገባውም አለ።
15:3b.1CH.015.003ዳዊትም ወዳዘጋጀለት ስፍራ የእግዚአብሔርን ታቦት ያመጣ ዘንድ እስራኤልን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
15:4b.1CH.015.004ዳዊትም የአሮንን ልጆችና ሌዋውያንን ሰበሰበ።
15:5b.1CH.015.005ከቀዓት ልጆች፤ አለቃው ኡርኤል፥ ወንድሞቹም መቶ ሀያ፤
15:6b.1CH.015.006ከሜራሪ ልጆች፤ አለቃው ዓሣያ፥ ወንድሞቹም ሁለት መቶ ሀያ፤
15:7b.1CH.015.007ከጌድሶን ልጆች፤ አለቃው ኢዮኤል፥ ወንድሞቹም መቶ ሠላሳ፤
15:8b.1CH.015.008ከኤሊጻፋን ልጆች፤ አለቃው ሸማያ፥ ወንድሞቹም ሁለት መቶ፤
15:9b.1CH.015.009ከኬብሮን ልጆች፤ አለቃው ኤሊኤል፥ ወንድሞቹም ሰማንያ፤
15:10b.1CH.015.010ከዑዝኤል ልጆች፤ አለቃው አሚናዳብ፥ ወንድሞቹም መቶ አሥራ ሁለት።
15:11b.1CH.015.011ዳዊትም ካህናቱን ሳዶቅንና አቢያታርን፥ ሌዋውያንንም ኡርኤልን፥ ዓሣያን፥ ኢዮኤልን፥ ሸማያን፥ ኤሊኤልን፥ አሚናዳብንም ጠርቶ።
15:12b.1CH.015.012እናንተ የሌዋውያን አባቶች ቤቶች አለቆች ናችሁ፤ ወዳዘጋጀሁለት ስፍራ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ታመጡ ዘንድ እናንተና ወንድሞቻችሁ ተቀደሱ።
15:13b.1CH.015.013ቀድሞም አልተሸከማችሁምና፥ እንደ ሥርዓቱም አልፈለግነውምና አምላካችን እግዚአብሔር በመካከላችን ስብራት አደረገ አላቸው።
15:14b.1CH.015.014የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርን ታቦት ያመጡ ዘንድ ካህናቱና ሌዋውያኑ ተቀደሱ።
15:15b.1CH.015.015ሙሴም እንዳዘዘው እንደ እግዚአብሔር ቃል የሌዋውያን ልጆች የእግዚአብሔርን ታቦት በትከሻቸው ላይ በመሎጊያዎቹ ተሸከሙ።
15:16b.1CH.015.016ዳዊትም በዜማ ዕቃ በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን ወንድሞቻቸውን ይሾሙ ዘንድ ለሌዋውያን ኣለቆች ተናገረ።
15:17b.1CH.015.017ሌዋውያኑም የኢዮኤልን ልጅ ኤማንን፥ ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፥ ከወንድሞቻቸውም ከሜራሪ ልጆች የቂሳን ልጅ ኤታንን፥
15:18b.1CH.015.018ከእነርሱም ጋር በሁለተኛው ተራ የሆኑትን ወንድሞቻቸውን ዘካርያስን፥ ቤንን፥ ያዝኤልን፥ ሰሚራሞትን፥ ይሒኤልን፥ ዑኒን፥ ኤልያብን፥ በናያስን፥ መዕሤያን፥ መቲትያን፥ ኤሊፍሌሁን፥ ሚቅንያን፥ በረኞችንም ዖቤድኤዶምንና ይዒኤልን አቆሙ።
15:19b.1CH.015.019መዘምራንም ኤማንና አሳፍ ኤታንም በናስ ጸናጽል ከፍ አድርገው ያሰሙ ነበር።
15:20b.1CH.015.020ዘካርያስ፥ ዓዝዔል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ ዑኒ፥ ኤልያብ፥ መዕሤያ፥ በናያስ በመሰንቆ ምሥጢር ነገር ያዜሙ ነበር።
15:21b.1CH.015.021መቲትያ፥ ኤልፍሌሁ፥ ሚቅኒያ፥ ዖቤድኤዶም፥ ይዒኤል፥ ዓዛዝያ ስምንት አውታር ባለው በገና ይዘምሩ ነበር።
15:22b.1CH.015.022የሌዋውያኑም አለቃ ክናንያ በዜማ ላይ ተሹሞ ነበር። ብልሃተኛ ነበረና ዜማ ያስተምራቸው ነበር።
15:23b.1CH.015.023በራክያና ሕልቃናም ለታቦቱ በረኞች ነበሩ።
15:24b.1CH.015.024ካህናቱም ሰበንያ፥ ኢዮሳፍጥ፥ ናትናኤል፥ ዓማሣይ፥ ዘካርያስ፥ በናያስ፥ አልዓዛር በእግዚአብሔር ታቦይ ፊት መለከት ይነፉ ነበር። ዖቤድኤዶምና ይሒያም ለታቦቱ በረኞች ነበሩ።
15:25b.1CH.015.025ዳዊትም፥ የእስራኤልም ሽማግሌዎች፥ የሻለቆችም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከአቢዳራ ቤት በደስታ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።
15:26b.1CH.015.026የእግዚአብሔርንም ቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙትን ሌዋውያንን እግዚአብሔር በረዳቸው ጊዜ ሰባት በሬዎችና ሰባት አውራ በጎች ሰዉ።
15:27b.1CH.015.027ዳዊትም፥ ታቦቱንም የተሸከሙ ሌዋውያን ሁሉ፥ መዘምራኑም፥ የመዘምራኑም አለቃ ከናንያ የጥሩ በፍታ ቀሚስ ለብሰው ነበር፤ ዳዊትም የበፍታ ኤፉድ ነበረው።
15:28b.1CH.015.028እንዲሁ እስራኤል ሁሉ ሆ እያሉ ቀንደ መለከትና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽልና መሰንቆም በገናም እየመቱ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።
15:29b.1CH.015.029የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደረሰ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሡም ዳዊት ሲዘፍንና ሲጫወት አይታ በልቧ ናቀችው።
16
16:1b.1CH.016.001የእግዚአብሔርንም ታቦት ይዘው ገቡ፥ ዳዊትም በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕትም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ።
16:2b.1CH.016.002ዳዊትም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ማቅረብ በፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ስም ሕዝቡን ባረከ።
16:3b.1CH.016.003ለእስራኤልም ለወንዱም ለሴቱም ለእያንዳንዱ አንዳንድ እንጀራ፤ አንዳንድም ቍራጭ ሥጋ፥ አንዳንድም የዘቢብ ጥፍጥፍ አካፈለ።
16:4b.1CH.016.004በእግዚአብሔርም ታቦት ፊት ያገለግሉ ዘንድ፥ የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን ይወድሱት ዘንድ፥ ያመሰግኑትና ያከብሩትም ዘንድ ከሌዋውያን ወገን አቆመ።
16:5b.1CH.016.005አለቃው አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም በኋላ ዘካርያስ፥ ይዒኤል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ መቲትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ ዖቤድኤዶም፥ ይዒኤል በመሰንቆና በበገና አሳፍም በጸናጽል ይዘምሩ ነበር።
16:6b.1CH.016.006ካህናቱም በናያስና የሕዚኤል በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ሁልጊዜ መለከት ይነፉ ነበር።
16:7b.1CH.016.007በዚያም ቀን ዳዊት በአሳፍና በወንድሞቹ እጅ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ ትእዛዝን ሰጠ።
16:8b.1CH.016.008እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ስሙን ጥሩ፤ ለአሕዛብ ሥራውን አውሩ።
16:9b.1CH.016.009ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፤ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።
16:10b.1CH.016.010በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው።
16:11b.1CH.016.011እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።
16:12b.1CH.016.012ባሪያዎቹ የእስራኤል ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራትን ድንቅ አስቡ፥ ተአምራቱንም የአፉንም ፍርድ።
16:14b.1CH.016.014እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው። ቃል ኪዳኑን ለዘላለም፥ እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥
16:16b.1CH.016.016ለአብርሃም ያደረገውን፥ ለይስሐቅም የማለውን፤
16:17b.1CH.016.017ለያዕቆብ ሥርዓት እንዲሆን ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን እንዲሆን አጸና፤
16:18b.1CH.016.018እንዲህም አለ። ለአንተ የከነዓንን ምድር የርስታችሁን ገመድ እሰጣለሁ፤
16:19b.1CH.016.019ይህም የሆነው እነርሱ በቍጥር ጥቂቶች ሰዎች፥ እጅግ ጥቂቶችና ስደተኞች ሲሆኑ ነው።
16:20b.1CH.016.020ከሕዝብ ወደ ሕዝብ፥ ከመንግሥትም ወደ ሌላ ሕዝብ አለፉ።
16:21b.1CH.016.021የቀባኋቸውን አትዳስሱ፥ በነቢያቴም ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም፤ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።
16:23b.1CH.016.023ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ዕለት ዕለት ማዳኑን አውሩ።
16:24b.1CH.016.024ክብሩን ለአሕዛብ፥ ተአምራቱንም ለወገኖች ሁሉ ንገሩ።
16:25b.1CH.016.025እግዚአብሔር ታላቅ፥ ምስጋናውም ብዙ ነውና፤ በአማልክትም ሁሉ ላይ የተፈራ ነው።
16:26b.1CH.016.026የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
16:27b.1CH.016.027ክብርና ግርማ በፊቱ፥ ኃይልና ደስታ በስፍራው ውስጥ ናቸው።
16:28b.1CH.016.028የአሕዛብ ወገኖች ለእግዚአብሔር አምጡ፥ ክብርንና ኃይልን ለእግዚአብሔር አምጡ።
16:29b.1CH.016.029ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር አምጡ፤ ቍርባንን ይዛችሁ በፊቱ ግቡ፤ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
16:30b.1CH.016.030ምድር ሁሉ በፊቱ ትነዋወጥ፤ ዓለሙም እንዳይናወጥ ጸንቶአል።
16:31b.1CH.016.031ሰማያት ደስ ይበላቸው፥ ምድርም ሐሴትን ታድርግ፤ በአሕዛብም መካከል። እግዚአብሔር ነገሠ በሉ።
16:32b.1CH.016.032ባሕርና ሞላዋ ትናወጥ፤ በረሀ በእርሷም ያሉ ሁሉ ሐሤትን ያድርጉ።
16:33b.1CH.016.033በምድር ሊፈርድ ይመጣልና፥ የዱር ዛፎች በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይላቸዋል።
16:34b.1CH.016.034ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ።
16:35b.1CH.016.035የመዳናችን አምላክ ሆይ፥ አድነን፤ ቅዱስ ስምህን እናመሰግን ዘንድ፥ በምስጋናህም እንመካ ዘንድ፥ ከአሕዛብ ሰብስበህ ታደገን በሉ።
16:36b.1CH.016.036ከዘላለም እስከ ዘላለም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበሉ፤ እግዚአብሔርንም ያመስግኑ።
16:37b.1CH.016.037እንዲሁም በየቀኑ እንደሚገባቸው በታቦቱ ፊት ዘወትር ያገለግሉ ዘንድ አሳፍንና ወንድሞቹን፥ ዖቤድኤዶምንም፥ ስድሳ ስምንቱንም ወንድሞቻቸውን በዚያ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተዋቸው።
16:38b.1CH.016.038የኤዶታምም ልጅ ዖቤድኤዶምና ሖሳ በረኞች ይሆኑ ዘንድ ተዋቸው።
16:39b.1CH.016.039ካህኑም ሳዶቅንና ካህናቱን ወንድሞቹን በገባዖን በኮረብታው መስገጃ ባለው በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት አቆማቸው፥
16:40b.1CH.016.040ለእስራኤልም ባዘዘው በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈ ሁሉ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁል ጊዜ ጥዋትና ማታ ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ።
16:41b.1CH.016.041ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ኤማንንና ኤዶታምን፥ በስማቸውም የተጻፉትን ተመርጠው የቀሩትን ከእነርሱ ጋር አቆመ።
16:42b.1CH.016.042ከእነርሱም ጋር ካህናቱ ከፍ አድርገው ለማሰማት መለከትና ጸናጽል ለእግዚአብሔርም መዝሙራት የዜማ ዕቃ ይዘው ነበር፤ የኤዶታምም ልጆች በረኞች ነበሩ።
16:43b.1CH.016.043ሕዝቡ ሁሉ እያንዳንዱ ወደ ቤቱ ሄደ፤ ዳዊትም ቤቱን ይባርክ ዘንድ ተመለሰ።
17
17:1b.1CH.017.001እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩን ናታንን። እነሆ፥ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጫለሁ፤ የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት በመጋረጃዎች ውስጥ ተቀምጦአል አለው።
17:2b.1CH.017.002ናታንም ዳዊትን። እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና በልብህ ያለውን ሁሉ አድርግ አለው።
17:3b.1CH.017.003በዚያም ሌሊት የእግዚአብሔር ቃል ወደ ናታን መጣ እንዲህም አለው።
17:4b.1CH.017.004ሂድ፥ ለባሪያዬ ለዳዊት ንገረው። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እስራኤልን ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከድንኳን ወደ ድንኳን፥ ከማደሪያም ወደ ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርሁምና የምኖርበትን ቤት አትሠራልኝም።
17:6b.1CH.017.006ከእስራኤል ሁሉ ጋር ባለፍሁበት ስፍራ ሁሉ። ስለ ምን ቤትን ከዝግባ እንጨት አልሠራችሁልኝም? ብዬ ሕዝቤን ይጠብቅ ዘንድ ከእስራኤል ፈራጆች ላዘዝሁት ለአንዱ በውኑ ተናግሬአለሁን?
17:7b.1CH.017.007አሁንም ባሪያዬን ዳዊትን እንዲህ በለው። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። አንተ መንጋውን ስትከተል በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰድሁህ።
17:8b.1CH.017.008በሄድህበትም ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁ፤ በምድርም ላይ እንዳሉ እንደታላላቆች ስም ለአንተ ስም አደርጋለሁ።
17:9b.1CH.017.009ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርግለታለሁ፥ እተክለውማለሁ፥ በስፍራውም ይቀመጣል፥ ከዚያም በኋላ አይናወጥም፤ እንደቀድሞው ዘመንና በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ፈራጆች እንዳስነሣሁበት ጊዜ ግፈኞች ተመልሰው አያስጨንቁትም፤ ጠላቶችህንም ሁሉ አዋርዳቸዋለሁ። እግዚአብሔር ደግሞ ቤት እንዲሠራልህ እነግርሃለሁ።
17:11b.1CH.017.011ወደ አባቶችህም ትሄድ ዘንድ ዕድሜህ በተፈጸመ ጊዜ ከልጆችህ የሚሆነውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።
17:12b.1CH.017.012እርሱ ቤት ይሠራልኛል፤ ዙፋኑንም ለዘላለም አጸናለሁ።
17:13b.1CH.017.013እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ከአንተ አስቀድሞ ከነበረው እንዳራቅሁ፥ ምሕረቴን ከእርሱ አላርቅም።
17:14b.1CH.017.014በቤቴና በመንግሥቴም ለዘላለም አቆመዋለሁ፤ ዙፋኑም ለዘላለም ይጸናል።
17:15b.1CH.017.015እንደዚህ ነገር ሁሉ እንደዚህም ራእይ ሁሉ ናታን ለዳዊት ነገረው።
17:16b.1CH.017.016ንጉሡም ዳዊት ገባ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ተቀምጦ እንዲህ አለ። አቤቱ አምላክ ሆይ፥ እስከዚህ ያደረስኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምንድር ነው?
17:17b.1CH.017.017አምላክ ሆይ ይህ በፊትህ ጥቂት ነበረ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ስለ ባሪያህ ቤት ደግሞ ለሩቅ ዘመን ተናገርህ፤ እንደ አንድ ባለ ማዕርግ ሰው ተመለከትኸኝ።
17:18b.1CH.017.018አንተ ባሪያህን ታውቀዋለህና ለባሪያህ ስለ ተደረገ ክብር ዳዊት ጨምሮ የሚለው ምንድር ነው?
17:19b.1CH.017.019አቤቱ፥ ይህን ታላቅ ነገር ሁሉ ታስታውቀው ዘንድ ስለ ባሪያህ እንደ ልብህም ይህን ታአምራት ሁሉ አድርገሃል።
17:20b.1CH.017.020አቤቱ፥ እንዳንተ ያለ የለም፥ በጆሮአችንም እንደሰማን ሁሉ ከአንተ በቀር አምላክ የለም።
17:21b.1CH.017.021አንተ እግዚአብሔር ከግብጽ ካወጣኸው ከሕዝብህ ፊት አሕዛብን በማሳደድ በታላቅና በሚያስፈራ ነገር ለአንተ ስም ታደርግ ዘንድ፥ ለአንተም ሕዝብ ትቤዥ ዘንድ እንደሄድህለት እንዳንተ ሕዝብ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ሌላ ሕዝብ አለን?
17:22b.1CH.017.022ሕዝብህንም እስራኤልን ለዘላለም ሕዝብህ አደረግኸው፤ አንተም፥ አቤቱ፥ አምላክ ሆነኸዋል።
17:23b.1CH.017.023አሁንም፥ አቤቱ፥ ስለ ባሪያህና ስለ ቤቱ የተናገርኸው ለዘላለም የጸና ይሁን፤ እንደተናገርህም አድርግ።
17:24b.1CH.017.024የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እርሱ የእስራኤል አምላክ ነው፥ በእውነት የእስራኤል አምላክ ነው ይባል ዘንድ ስምህ ለዘላለም ጽኑና ታላቅ ይሁን፤ የባሪያህም የዳዊት ቤት በፊትህ ጸንቶአል።
17:25b.1CH.017.025አምላኬ ሆይ፥ ቤት እንድሠራለት ለባሪያህ ገልጠሃልና ስለዚህ ባሪያህ ወዳንተ ይጸልይ ዘንድ በልቡ ደፈረ።
17:26b.1CH.017.026አሁንም፥ አቤቱ፥ አንተ አምላክ ነህ፥ ይህንም መልካም ነገር ለባሪያህ ተናግረሃል።
17:27b.1CH.017.027አሁንም በፊትህ ለዘላለም ይኖር ዘንድ የባሪያህን ቤት እንድትባርክ ፈቅደሃል፤ አንተም፥ አቤቱ፥ ባርከኸዋል፥ ለዘላለምም ቡሩክ ይሆናል።
18
18:1b.1CH.018.001ከዚህም በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታ፥ አዋረዳቸውም፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ጌትንና መንደሮችዋን ወሰደ።
18:2b.1CH.018.002ሞዓብን መታ፤ ሞዓባውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት።
18:3b.1CH.018.003ዳዊትም በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ የነበረውን ግዛት ለመያዝ በሄደ ጊዜ የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን እስከ ሃማት ድረስ መታ።
18:4b.1CH.018.004ዳዊትም ከእርሱ አንድ ሺህ ሰረገሎች፥ ሰባት ሺህም ፈረሰኞች፥ ሀያ ሺህም እግረኞች ወሰደ፤ ዳዊት ለመቶ ሰረገሎች የሚሆኑትን ብቻ አስቀርቶ የሰረገሎቹን ፈረሶች ቋንጃ ቆረጠ።
18:5b.1CH.018.005ከደማስቆም ሶርያውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ሊረዱ በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶርያውያን ሀያ ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደለ።
18:6b.1CH.018.006ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ ጭፍሮች አኖረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ ግብርም አመጡለት። እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድል ይሰጠው ነበር።
18:7b.1CH.018.007ዳዊትም ለአድርአዛር ባሪያዎች የነበሩትን የወርቅ ጋሻዎች ወሰደ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም ይዞአቸው መጣ።
18:8b.1CH.018.008ከአድርአዛርም ከተሞች ከጢብሐትና ከኩን ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፤ ከዚህም ሰሎሞን የናሱን ኵሬና ዓምዶች የናሱንም ዕቃ ሠራ።
18:9b.1CH.018.009የሐማትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱባን ንጉሥ የአድርአዛርን ጭፍራ ሁሉ እንደ መታ ሰማ።
18:10b.1CH.018.010ቶዑም ከአድርአዛር ጋር ሁል ጊዜ ይዋጋ ነበርና ዳዊት አድርአዛርን ወግቶ ስለመታው ደኅንነቱን ይጠይቅ ዘንድ ይመርቀውም ዘንድ ልጁን አዶራምን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የወርቅና የብር የናስም ዕቃ ይዞ መጣ።
18:11b.1CH.018.011ንጉሡም ዳዊት ከአሕዛብ ሁሉ ከኤዶምና ከሞዓብ ከአሞንም ልጆች ከፍልስጥኤማውያንም ከአማሌቅም ከማረከው ብርና ወርቅ ጋር እነዚህን ደግሞ ለእግዚአብሔር ቀደሰ።
18:12b.1CH.018.012ደግሞ የጽሩያ ልጅ አቢሳ ከኤዶማውያን በጨው ሸለቆ ውስጥ አሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች ገደለ።
18:13b.1CH.018.013በኤዶምያስም ጭፍሮች አኖረ፥ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ገባሮች ሆኑ። እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድል ይሰጠው ነበር።
18:14b.1CH.018.014ዳዊትም በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ለሕዝቡም ሁሉ ፍርድንና ጽድቅም አደረገላቸው።
18:15b.1CH.018.015የጽሩያ ልጅ ኢዮአብም የሠራዊት አለቃ ነበረ፤ የአሒሉድም ልጅ ኢዮሣፍጥ ታሪክ ጸሐፊ ነበረ።
18:16b.1CH.018.016የአኪጦብም ልጅ ሳዶቅ፥ የአቤሜሌክም ልጅ አብያታር ካህናት ነበሩ፤ ሱሳ ጸሐፊ ነበረ።
18:17b.1CH.018.017የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፤ የዳዊትም ልጆች በንጉሡ አጠገብ አለቆች ነበሩ።
19
19:1b.1CH.019.001ከዚህም በኋላ የአሞን ልጆች ንጉሥ ናዖስ ሞተ፥ ልጁም በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
19:2b.1CH.019.002ዳዊትም። አባቱ ስላደረገልኝ ወረታ እኔ ለናዖስ ልጅ ለሐኖን ቸርነት አደርጋለሁ አለ። ዳዊትም አባቱ ስለ ሞተ ልያጽናናው መልእክተኞችን ላከ፤ የዳዊትም ባሪያዎች ሊያጽናኑት ወደ ሐኖን ወደ አሞን ልጆች ምድር መጡ።
19:3b.1CH.019.003የአሞን ልጆች አለቆች ግን ሐኖንን። ዳዊት አባትህን አክብሮ የሚያጽናኑህን ወደ አንተ የላከ ይመስልሃልን? ባሪያዎቹስ አገሪቱን ለመመርመር፥ ለማጥፋት፥ ለመሰለልም ወደ አንተ የመጡ አይደሉምን? አሉት።
19:4b.1CH.019.004ሐኖንም የዳዊትን ባሪያዎች ወስዶ አስላጫቸው፥ ልብሳቸውንም እስከ ወገባቸው ድረስ ከሁለት ቀድዶ ሰደዳቸው።
19:5b.1CH.019.005ወሬኞችም ሄደው በሰዎቹ ላይ የተደረገውን ለዳዊት አስታወቁት። ሰዎቹም በብዙ አፍረዋልና ተቀባዮች ላከ፤ ንጉሡም። ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ ተቀመጡ፥ ከዚያም በኋላ ተመለሱ አለ።
19:6b.1CH.019.006የአሞንም ልጆች በዳዊት ዘንድ እንደ ተጠሉ ባዩ ጊዜ ሐኖንና የአሞን ልጆች ከመስጴጦምያ፥ ከአራምመዓካ፥ ከሱባ ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን ይቀጥሩ ዘንድ አንድ ሺህ መክሊት ብር ላኩ።
19:7b.1CH.019.007ሠላሳ ሁለትም ሺህ ሰረገሎች የመዓካንም ንጉሥ ሕዝቡንም ቀጠሩ፤ መጥተውም በሜድባ ፊት ለፊት ሰፈሩ። የአሞንም ልጆች ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ወደ ሰልፍ መጡ።
19:8b.1CH.019.008ዳዊትም ይህ በሰማ ጊዜ ኢዮአብንና የኃያላኑን ሠራዊት ሁሉ ላከ።
19:9b.1CH.019.009የአሞንም ልጆች ወጥተው በከተማይቱ በር አጠገብ ተሰለፉ፤ የመጡትም ነገሥታት ለብቻቸው በሜዳው ላይ በሩ።
19:10b.1CH.019.010ኢዮአብም በፊትና በኋላ ሰልፍ እንደ ከበበው ባየ ጊዜ ከእስራኤል ምርጥ ምርጦችን ሁሉ ለይቶ በሶርያውያን ላይ አሰለፋቸው።
19:11b.1CH.019.011የቀረውንም ሕዝብ ለወንድሙ ለአቢሳ ሰጠው፥ በአሞንም ልጆች ላይ ተሰለፉ።
19:12b.1CH.019.012እርሱም። ሶርያውያን ቢበረቱብኝ እርዳኝ፤ የአሞንም ልጆች ቢበረቱብህ እረዳሃለሁ።
19:13b.1CH.019.013አይዞህ፥ ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንበርታ፤ እግዚአብሔርም ደስ ያሰኘውን ያድርግ አለ።
19:14b.1CH.019.014ኢዮአብና ከእርሱም ጋር የነበረው ሕዝብ ለሰልፍ ወደ ሶርያውያን ፊት ቀረቡ፥ እነርሱም ከፊቱ ሸሹ።
19:15b.1CH.019.015የአሞንም ልጆች ሶርያውያን እንደ ሸሹ ባዩ ጊዜ እነርሱ ደግሞ ከወንድሙ ከአቢሳ ፊት ሸሹ፥ ወደ ከተማይቱም ገቡ። ኢዮአብም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።
19:16b.1CH.019.016ሶርያውያንም በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ መልእክተኞች ልከው በወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን አስመጡ፤ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሾፋክ በፊታቸው ነበረ።
19:17b.1CH.019.017ዳዊትም በሰማ ጊዜ እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፥ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ መጣባቸው፥ ከእነርሱም ጋር ተዋጋ፤ ዳዊትም በሶርያውያን ላይ በተሰለፈ ጊዜ እነርሱ ከእርሱ ጋር ተዋጉ።
19:18b.1CH.019.018ሶርያውያንም ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ሰባት ሺህ ሰረገለኞች፥ አርባ ሺህም እግረኞች ገደለ፥ የሠራዊቱንም አለቃ ሾፋክን ገደለ።
19:19b.1CH.019.019የአድርአዛርም ባሪያዎች በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ ከዳዊት ጋር ታረቁ፥ ገበሩለትም፤ ሶርያውያንም ከዚያ ወዲያ የአሞንን ልጆች ይረዱ ዘንድ እንቢ አሉ።
20
20:1b.1CH.020.001እንዲህም ሆነ፤ በዓመት መለወጫ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ ኢዮአብ ሠራዊቱን አወጣ፥ የአሞንንም ልጆች አገር አጠፋ፤ መጥቶም ረባትን ከበበ። ዳዊትም በኢየሩሳሌም ቈይቶ ነበር።
20:2b.1CH.020.002ኢዮአብም ረባትን መትቶ አፈረሳት። ዳዊትም የንጉሣቸውን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፥ ክብደቱም አንድ መክሊት ወርቅ ያህል ነበረ፥ ክቡርም ዕንቍ ነበረበት፥ በዳዊትም ራስ ላይ አስቀመጡት፤ ከከተማይቱም እጅግ ብዙ ምርኮ አወጣ።
20:3b.1CH.020.003በውስጥዋም የነበረውን ሕዝብ አውጥቶ በመጋዝና በብረት መቈፈሪያ በመጥረቢያም እንዲሠሩ አደረጋቸው። እንዲሁም ዳዊት በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ አደረገ። ዳዊትም ሕዝቡም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
20:4b.1CH.020.004ከዚህም በኋላ በጌዝር ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ሆነ፤ ኩሳታዊውም ሴቦካይ ከራፋይም ወገን የነበረውን ሲፋይን ገደለ።
20:5b.1CH.020.005ደግሞም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ፤ የያዒርም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው የጎልያድን ወንድም ለሕሚን ገደለ።
20:6b.1CH.020.006ደግሞ በጌት ላይ ሰልፍ ነበረ፤ ከዚያም በእጁና በእግሩ ስድስት ስድስት ሁላሁሉ ሀያ አራት ጣቶች ያሉት አንድ ረጅም ሰው ነበረ፤ እርሱም ደግሞ ከራፋይም የተወለደ ነበረ።
20:7b.1CH.020.007እስራኤልንም በተገዳደረ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ዮናታን ገደለው።
20:8b.1CH.020.008እነዚያም በጌት ውስጥ ከራፋይም የተወለዱ ነበሩ፤ በዳዊትም እጅ በባሪያዎቹም እጅ ወደቁ።
21
21:1b.1CH.021.001ሰይጣንም በእስራኤል ላይ ተነሣ፥ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን አንቀሳቀሰው።
21:2b.1CH.021.002ዳዊትም ኢዮአብንና የሕዝቡን አለቆች። ሂዱ፥ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ እስራኤልን ቍጠሩ፥ ድምራቸውንም አውቅ ዘንድ አስታውቁኝ አላቸው።
21:3b.1CH.021.003ኢዮአብም። እግዚአብሔር ሕዝቡን በአሁኑ ላይ መቶ እጥፍ ይጨምር፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ሁሉ የጌታዬ ባሪያዎች አይደሉምን? ይህን ነገር ጌታዬ ለምን ይሻል? በእስራኤል ላይ በደል ስለ ምን ያመጣል?
21:4b.1CH.021.004ነገር ግን የንጉሡ ቃል በኢዮአብ ላይ አሸነፈ፤ ኢዮአብም ወጥቶ በእስራኤል ሁሉ ላይ ተዘዋወረ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም መጣ።
21:5b.1CH.021.005ኢዮአብም የቈጠራቸውን የሕዝቡን ድምር ለዳዊት ሰጠ፤ ከእስራኤልም ሁሉ አንድ ሚሊዮን ከመቶ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎችን አገኘ፤ ከይሁዳም አራት መቶ ሰባ ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎችን አገኘ።
21:6b.1CH.021.006የንጉሡ ትእዛዝ ግን በኢዮአብ ዘንድ የተጠላ ነበርና ሌዊና ብንያም ከእነርሱ ጋር አልተቈጠሩም።
21:7b.1CH.021.007ከዚህም ነገር የተነሣ እግዚአብሔር ተቈጣ፥ እስራኤልንም ቀሠፈ።
21:8b.1CH.021.008ዳዊትም እግዚአብሔርን። ይህን በማድረግ እጅግ በድያለሁ፤ አሁን ግን ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባሪያህን ኃጢአት ታስወግድ ዘንድ እለምንሃለሁ አለው።
21:9b.1CH.021.009እግዚአብሔርም ለዳዊት ባለ ራእይ ለጋድ።
21:10b.1CH.021.010ሂድ፥ ለዳዊት። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ሦስቱን ነገሮች በፊትህ አኖራለሁ፤ አደርግብህ ዘንድ ከእነርሱ አንዱን ምረጥ ብለህ ንገረው ብሎ ተናገረው።
21:11b.1CH.021.011ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የምትወድደውን ምረጥ፤
21:12b.1CH.021.012የሦስት ዓመት ራብ፥ ወይም ሦስት ወር የጠላቶችህ ሰይፍ እንዲያገኝህ ከጠላቶችህ መሰደድን፥ ወይም ሦስት ቀን የእግዚአብሔር ሰይፍ ቸነፈርም በምድር ላይ መሆንን፥ የእግዚአብሔርም መልአክ በእስራኤል ምድር ሁሉ ማጥፋትን ምረጥ፤ አሁንም ለላከኝ ምን እንድመልስ ተመልከት አለው።
21:13b.1CH.021.013ዳዊትም ጋድን። እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ምሕረቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ ልውደቅ፤ በሰው እጅ ግን አልውደቅ አለው።
21:14b.1CH.021.014እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ቸነፈርን ሰደደ፤ ከእስራኤልም ሰባ ሺህ ሰዎች ወደቁ።
21:15b.1CH.021.015እግዚአብሔርም ያጠፋት ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም መልአክን ሰደደ፤ ሊያጠፋትም በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር አይቶ ስለ ክፉው ነገር ተጸጸተ፥ የሚያጠፋውንም መልአክ። በቃህ፤ አሁን እጅህን መልስ አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
21:16b.1CH.021.016ዳዊትም ዓይኖቹን አነሣ፤ የእግዚአብሔር መልአክ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተዘርግቶ አየ። ዳዊትም ሽማግሌዎችም ማቅ ለብሰው በግምባራቸው ተደፉ።
21:17b.1CH.021.017ዳዊትም እግዚአብሔርን። ሕዝቡ ይቈጠር ዘንድ ያዘዝሁ እኔ አይደለሁምን? የበደልሁና ክፉ የሠራሁ እኔ ነኝ፤ እነዚህ በጎች ግን ምን አድርገዋል? አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን፥ ነገር ግን ይቀሠፍ ዘንድ በሕዝብህ ላይ አትሁን አለው።
21:18b.1CH.021.018የእግዚአብሔርም መልአክ ዳዊት ወጥቶ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ላይ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራ ዘንድ ለዳዊት እንዲነግረው ጋድን አዘዘው።
21:19b.1CH.021.019ዳዊትም በእግዚአብሔር ስም እንደ ተናገረው እንደ ጋድ ነገር ወጣ።
21:20b.1CH.021.020ኦርናም ዘወር ብሎ መልአኩን አየ፥ ከእርሱም ጋር የነበሩ አራቱ ልጆቹ ተሸሸጉ፤ ኦርናም ስንዴ ያበራይ ነበር።
21:21b.1CH.021.021ዳዊትም ወደ ኦርና በመጣ ጊዜ ኦርና ተመልክቶ ዳዊትን አየ፤ ከአውድማውም ወጥቶ ዳዊትን እጅ ሊነሣ በምድር ላይ ተደፋ።
21:22b.1CH.021.022ዳዊትም ኦርናን። በላዩ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እሠራ ዘንድ ይህን የአውድማ ስፍራ ስጠኝ፤ በሙሉ ዋጋ ስጠኝ፤ መቅሠፍቱን ከሕዝቡ ይከለከላል አለው።
21:23b.1CH.021.023ኦርናም ዳዊትን። ለአንተ ውሰደው፥ ጌታዬ ንጉሡም ደስ የሚያሰኘውን ያድርግ፤ እነሆ፥ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሬዎቹን፥ ለእንጨትም የአውድማውን ዕቃ፥ ከእህልም ቍርባን ስንዴውን እሰጥሃለሁ፤ ሁሉን እሰጣለሁ አለው።
21:24b.1CH.021.024ንጉሡም ዳዊት ኦርናን። አይደለም፥ ነገር ግን ለአንተ ያለውን ለእግዚአብሔር አምጥቼ የሚቃጠል መሥዋዕት በከንቱ አላቀርብምና በሙሉ ዋጋ እገዛዋለሁ አለው።
21:25b.1CH.021.025ዳዊትም ስለ ስፍራው ስድስት መቶ ሰቅል ወርቅ በሚዛን ለኦርና ሰጠው።
21:26b.1CH.021.026ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ጠራ፤ ከሰማይም ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ በእሳት መለሰለት።
21:27b.1CH.021.027እግዚአብሔርም መልአኩን አዘዘው፥ ሰይፉንም በአፎቱ ከተተው።
21:28b.1CH.021.028በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ እንደ መለሰለት ዳዊት ባየ ጊዜ፥ በዚያ መሥዋዕት ሠዋ።
21:29b.1CH.021.029ሙሴም በምድረ በዳ የሠራት የእግዚአብሔር ማደሪያና ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነው መሠዊያ በዚያን ጊዜ በገባዖን ባለው በኮረብታው መስገጃ ነበሩ።
21:30b.1CH.021.030ዳዊት ግን የእግዚአብሔርን መልአክ ሰይፍ ስለ ፈራ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ወደዚያ ይሄድ ዘንድ አልቻለም።
22
22:1b.1CH.022.001ዳዊትም። ይህ የእግዚአብሔር ቤት ነው፥ ይህም ለእስራኤል ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነው መሠዊያ ነው አለ።
22:2b.1CH.022.002ዳዊትም በእስራኤል ምድር የነበሩትን መጻተኞች ይሰበስቡ ዘንድ አዘዘ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ለመሥራት የሚወቀሩትን ድንጋዮች ይወቅሩ ዘንድ ጠራቢዎችን አኖረ።
22:3b.1CH.022.003ዳዊትም ለበሮቹ ሳንቃ ለሚሆኑ ለምስማርና ለመጠረቂያ ብዙ ብረት፥ ከብዛቱም የተነሣ የማይመዘን ናስ አዘጋጀ።
22:4b.1CH.022.004ሲዶናውያውንና የጢሮስ ሰዎች ብዙ የዝግባ እንጨት ወደ ዳዊት ያመጡ ነበርና ቍጥር ያሌላቸውን የዝግባ እንጨቶች አዘጋጀ።
22:5b.1CH.022.005ዳዊትም። ልጄ ሰሎሞን ታናሽና ለጋ ብላቴና ነው፥ ለእግዚአብሔርም የሚሠራው ቤት እጅግ ማለፊያና በአገሩ ሁሉ ስሙና ክብሩ እንዲጠራ ይሆን ዘንድ ይገባል፤ ስለዚህ አዘጋጅለታለሁ አለ። ዳዊትም ሳይሞት አስቀድሞ ብዙ አዘጋጀ።
22:6b.1CH.022.006ልጁንም ሰሎሞንን ጠርቶ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ይሠራ ዘንድ አዘዘው።
22:7b.1CH.022.007ዳዊትም ሰሎሞንን እንዲህ አለ። ልጄ ሆይ፥ እኔ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ቤት እሠራ ዘንድ በልቤ አስቤ ነበር።
22:8b.1CH.022.008ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ። እጅግ ደም አፍስሰሃል፥ ታላቅም ሰልፍ አድርገሃል፤ በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም።
22:9b.1CH.022.009እነሆ፥ የዕረፍት ሰው የሚሆን ልጅ ይወለድልሃል፤ በዙሪያው ካሉ ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፈዋለሁ፤ ስሙ ሰሎሞን ይባላልና፥ በዘመኑም ሰላምንና ጸጥታን ለእስራኤል እሰጣለሁ።
22:10b.1CH.022.010እርሱ ለስሜ ቤት ይሠራል፥ ልጅም ይሆነኛል፥ እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ የመንግሥቱንም ዙፋን በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።
22:11b.1CH.022.011አሁንም፥ ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፤ ስለ አንተም እንደ ተናገረው ያከናውንልህ፥ የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ።
22:12b.1CH.022.012ብቻ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ሕግ ትጠብቅ ዘንድ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን ይስጥህ፥ በእስራኤልም ላይ ያሠልጥንህ።
22:13b.1CH.022.013እግዚአብሔር ስለ እስራኤል ሙሴን ያዘዘውን ሥርዓትና ፍርድ ታደርግ ዘንድ ብትጠነቀቅ በዚያን ጊዜ ይከናወንልሃል፤ አይዞህ፥ በርታ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥም።
22:14b.1CH.022.014አሁንም፥ እነሆ፥ በድህነቴ ለእግዚአብሔር ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ ሚዛንም የሌላቸው ብዙ ናስና ብረት አዘጋጀሁ፤ ደግሞም እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጀሁ፥ አንተም ከዚያ በላይ ጨምር።
22:15b.1CH.022.015በአንተም ዘንድ ብዙ ሠራተኞች፥ ድንጋይና እንጨት ወቃሪዎችና ጠራቢዎች፥ ሥራውንም ሁሉ ለማድረግ ጠቢባን ሰዎች ሁሉ አሉ።
22:16b.1CH.022.016የሚሠሩበት ወርቅና ብር ናስና ብረት ቍጥር የለውም፤ ተነሥተህ ሥራ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን።
22:17b.1CH.022.017ዳዊትም ደግሞ ልጁን ሰሎሞንን ያግዙ ዘንድ የእስራኤልን አለቆች ሁሉ እንዲህ ሲል አዘዛቸው።
22:18b.1CH.022.018አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይደለምን? በምድርም የሚቀመጡትን በእጄ አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ምድርም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ፊት ተገዝታለችና በዙሪያችሁ ሁሉ ዕረፍትን ሰጥቶአችኋል።
22:19b.1CH.022.019አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትፈልጉ ዘንድ ልባችሁንና ነፍሳችሁን ስጡ፤ ለእግዚአብሔርም ስም ወደሚሠራው ቤት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦትና የእግዚአብሔርን ንዋየ ቅድሳት ታመጡ ዘንድ ተነሥታችሁ የአምላክን የእግዚአብሔርን መቅደስ ሥሩ።
23
23:1b.1CH.023.001ዳዊትም በሸመገለ ጊዜ፥ ዕድሜንም በጠገበ ጊዜ ልጁን ሰሎሞንን በእስራኤል ላይ አነገሠው።
23:2b.1CH.023.002የእስራኤልንም አለቆች ሁሉ፥ ካህናቱንም፥ ሌዋውያኑንም ሰበሰበ።
23:3b.1CH.023.003ሌዋውያንም ከሠላሳ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ ተቈጠሩ፤ ቍጥራቸው በእያንዳንዱ ነፍስ ወከፍ ሠላሳ ስምንት ሺህ ነበረ።
23:4b.1CH.023.004ከእነዚህም ውስጥ የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ የሚያሠሩት ሀያ አራት ሺህ ነበሩ፤ ስድስቱ ሺህም አለቆችና ፈራጆች ነበሩ።
23:5b.1CH.023.005አራቱ ሺህም በረኞች ነበሩ፤ አራቱ ሺህም ለምስጋና በተሠሩት በዜማ ዕቃዎች እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።
23:6b.1CH.023.006ዳዊትም እንደ ሌዊ ልጆች እንደ ጌድሶንና እንደ ቀዓት እነደ ሜራሪም በየሰሞናቸው ከፈላቸው።
23:7b.1CH.023.007ከጌድሶናውያን ለአዳንና ሰሜኢ ነበሩ።
23:8b.1CH.023.008የለአዳን ልጆች አለቃው ይሒኤል፥ ዜቶም፥ ኢዮኤል ሦስት ነበሩ።
23:9b.1CH.023.009የሰሜኢ ልጆች ሰሎሚት፥ ሐዝኤል፥ ሐራን ሦስት ነበሩ። እነዚህ የለአዳን አባቶች ቤቶች አለቆች ነበሩ።
23:10b.1CH.023.010የሰሜኢ ልጆች ኢኢት፥ ዚዛ፥ የዑስ፥ በሪዓ ነበሩ። እነዚህ አራቱ የሰሜኢ ልጆች ነበሩ።
23:11b.1CH.023.011አለቃው ኢኢት ነበረ፤ ሁለተኛው ዚዛ ነበረ፤ የዑስና በሪዓ ግን ብዙ ልጆች አልነበሩአቸውም፤ ስለዚህ እንደ አንድ አባት ቤት ሆነው ተቈጠሩ።
23:12b.1CH.023.012የቀአት ልጆች እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል አራት ነበሩ።
23:13b.1CH.023.013የእንበረም ልጆች አሮንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮንም ከሁሉ በላይ የተቀደሰ ይሆን ዘንድ ተለየ፥ እርሱና ልጆቹ፥ ለዘላለም በእግዚአብሔር ፊት ያጥንና ያገለግል ዘንድ፥ በስሙም ለዘላለም ይባርክ ዘንድ።
23:14b.1CH.023.014የእግዚአብሔርም ሰው የሙሴ ልጆች በሌዊ ነገድ ተቈጠሩ።
23:15b.1CH.023.015የሙሴ ልጆች ጌርሳምና አልዓዛር ነበሩ።
23:16b.1CH.023.016የጌርሳም ልጆች አለቃ ሱባኤል ነበረ።
23:17b.1CH.023.017የአልዓዛርም ልጆች አለቃ ረዓብያ ነበረ፤ አልዓዛርም ሌሎች ልጆች አልነበሩትም፤ የረዓብያ ልጆች እጅግ ብዙ ነበሩ።
23:18b.1CH.023.018የይስዓር ልጆች አለቃው ሰሎሚት ነበረ።
23:19b.1CH.023.019የኬብሮን ልጆች አለቃው ይሪያ፥ ሁለተኛው አማርያ፥ ሦስተኛው የሕዚኤል፥ አራተኛው ይቅምዓም ነበሩ።
23:20b.1CH.023.020የዑዝኤል ልጆች አለቃው ሚካ፥ ሁለተኛው ይሺያ ነበሩ።
23:21b.1CH.023.021የሜራሪ ልጆች ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ። የሞሖሊ ልጆች አልዓዛርና ቂስ ነበሩ።
23:22b.1CH.023.022አልዓዛርም ሴቶች ልጆች ብቻ እንጂ ወንዶች ልጆች ሳይወልድ ሞተ፤ ወንድሞቻቸውም የቂስ ልጆች አገቡአቸው።
23:23b.1CH.023.023የሙሲ ልጆች ሞሖሊ፥ ዔደር፥ ኢያሪሙት ሦስት ነበሩ።
23:24b.1CH.023.024የእግዚአብሔርን ቤት አገልግሎት በሠሩ ከሀያ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ በነበሩ በእያንዳንዳቸው በስማቸው በተቆጠሩት ላይ የአባቶች ቤት አለቆች የሆኑት በየአባቶቻቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነዚህ ነበሩ።
23:25b.1CH.023.025ዳዊትም። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ዕረፍት ሰጥቶአል፥ በኢየሩሳሌምም ለዘላለም የቀመጣል።
23:26b.1CH.023.026ሌዋውያንም ከእንግዲህ ወዲህ ማደሪያውንና የማገልገያውን ዕቃ ሁሉ አይሸከሙም አለ።
23:27b.1CH.023.027በመጨረሻውም በዳዊት ትእዛዝ ከሀያ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት የሌዊ ልጆች ተቈጠሩ።
23:28b.1CH.023.028ሥራቸውም የእግዚአብሔርን ቤት በየአደባባዩና በየጓዳው ውስጥ ለማገልገል፥ ቅዱሱንም ዕቃ ሁሉ ለማንጻት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት አገልግሎት ለመሥራት ከአሮን ልጆች እጅ በታች ነበረ።
23:29b.1CH.023.029ደግሞም ገጸ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም፥ ለእህል ቍርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በልክ ሁሉ ያገለግሉ ነበር።
23:30b.1CH.023.030ሥራቸውም በየጥዋቱና በየማታው ቆመው እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለማክበር፥
23:31b.1CH.023.031በየሰንበታቱም በየመባቻዎቹም በየበዓላቱም እንደ ሥርዓቱ ቍጥር በእግዚአብሔር ፊት ዘወትር ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ ለማቅረብ፥
23:32b.1CH.023.032ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የመገናኛውን ድንኳን ሥርዓት የመቅደሱንም ሥርዓት የወንድሞቻቸውንም የአሮንን ልጆች ሥርዓት ለመጠበቅ ነበረ።
24
24:1b.1CH.024.001የአሮንም ልጆች ሰሞን ይህ ነው። የአሮን ልጆች ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ።
24:2b.1CH.024.002ናዳብና አብዩድ ግን ልጆች ሳይወልዱ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤ አልዓዛርና ኢታምርም ካህናት ሆኑ።
24:3b.1CH.024.003ዳዊትም ከአልዓዛር ልጆች ከሳዶቅ ጋር፥ ከኢታምርም ልጆች ከአቢሜሌክ ጋር ሆኖ እንደ አገልግሎታቸው ሥርዓት ከፍሎ መደባቸው።
24:4b.1CH.024.004የአልዓዛርም ልጆች አለቆች ከኢታምርም ልጆች አለቆች በልጠው ተገኙ፤ እንዲህም ተመደቡ፤ ከአልዓዛር ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች አሥራ ስድስት፥ ከኢታምርም ልጆች እንደ አባቶቻቸው ቤቶች ስምንት አለቆች ነበሩ።
24:5b.1CH.024.005ከአልዓዛርና ከኢታምርም ልጆች መካከል የመቅደሱና የእግዚአብሔር አለቆች ነበሩና እነዚህና እነዚያ እንዲህ በዕጣ ተመደቡ።
24:6b.1CH.024.006ከሌዋውያንም ወገን የነበረው የናትናኤል ልጅ ጸሐፊው ሸማያ በንጉሡና በአለቆቹ ፊት፥ በካህኑ በሳዶቅና በአብያታርም ልጅ በአቢሜሌክ ፊት፥ በካህናቱና በሌዋውያኑ አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት ጻፋቸው፤ አንዱንም የአባት ቤት ለአልዓዛር፥ አንዱንም ለኢታምር ጻፈ።
24:7b.1CH.024.007መጀመሪያውም ዕጣ ለዮአሪብ ወጣ፥ ሁለተኛው ለዮዳኤ፥
24:8b.1CH.024.008ሦስተኛው ለካሪም፥
24:9b.1CH.024.009አራተኛው ለሥዖሪም፥ አምስተኛው ለመልክያ፥
24:10b.1CH.024.010ስድስተኛው ለሚያሚን፥ ሰባተኛው ለአቆስ፥
24:11b.1CH.024.011ስምንተኛው ለአብያ፥ ዘጠኝኛው ለኢያሱ፥
24:12b.1CH.024.012አሥረኛው ለሴኬንያ፥ አሥራ አንደኛው ለኤልያሴብ፥ አሥራ ሁለተኛው ለያቂም፥
24:13b.1CH.024.013አሥራ ሦስተኛው ለኦፓ፥ አሥራ አራተኛው ለየሼብአብ፥
24:14b.1CH.024.014አሥራ አምስተኛው ለቢልጋ፥ አሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፥
24:15b.1CH.024.015አሥራ ሰባተኛው ለኤዚር፥ አሥራ ስምንተኛው ለሃፊጼጽ፥
24:16b.1CH.024.016አሥራ ዘጠኝኛው ለፈታያ፥
24:17b.1CH.024.017ሀያኛው ለኤዜቄል፥ ሀያ አንደኛው ለያኪን፥ ሀያ ሁለተኛው ለጋሙል፥
24:18b.1CH.024.018ሀያ ሦስተኛው ለድላያ፥ ሀያ አራተኛው ለመዓዝያ።
24:19b.1CH.024.019የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ አባታቸው አሮን እንደ ሰጣቸው ሥርዓት ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገቡበት የአገልግሎታቸው ሥርዓት ይህ ነበረ።
24:20b.1CH.024.020ከቀሩትም የሌዊ ልጆች፤ ከእንበረም ልጆች ሱባኤል፤ ከሱባኤል ልጆች ዬሕድያ፤
24:21b.1CH.024.021ከረዓብያ ልጆች አለቃው ይሺያ፤ ከይስዓራውያን ሰሎሚት፤ ከሰሎሚት ልጆች ያሐት፤
24:23b.1CH.024.023ከኬብሮንም ልጆች አለቃው ይሪያ፥ ሁለተኛው አማርያ፥ ሦስተኛው የሕዚኤል፥ አራተኛው ይቀምዓም፤
24:24b.1CH.024.024የዑዝኤል ልጅ ሚካ፤
24:25b.1CH.024.025የሚካ ልጅ ሻሚር፤ የሚካ ወንድም ይሺያ፤
24:26b.1CH.024.026ከይሺያ ልጆች ዘካርያስ፤ የሜራሪ ልጆች ሞሖሊ፥ ሙሲ፤ ከያዝያ ልጅ በኖ፤
24:27b.1CH.024.027የሜራሪ ልጆች፤ ከያዝያ በኖ፥ ሾሃም፥ ዘኩር፥ ዔብሪ፤
24:28b.1CH.024.028ከሞሖሊ አልዓዛር፥ እርሱም ልጆች አልነበሩት፤
24:29b.1CH.024.029ከቂስ፤ የቂስ ልጅ ይረሕምኤል፤ የሙሲም ልጆች፤ ሞሖሊ፥ ዔዳር፥ ኢያሪሙት።
24:30b.1CH.024.030እነዚህ እንደ አባቶቻቸው ቤቶች የሌዋውያን ልጆች ነበሩ።
24:31b.1CH.024.031እነዚህም ደግሞ በንጉሡ በዳዊትና በሳዶቅ በአቢሜሌክም በሌዋውያንና በካህናት አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት፥ ታላቁም እንደ ታናሹ፥ እንደ ወንድሞቻቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣጣሉ።
25
25:1b.1CH.025.001ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ የሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።
25:2b.1CH.025.002ከአሳፍ ልጆች፤ ዘኩር፥ ዮሴፍ፥ ነታንያ፥ አሸርኤላ፤ እነዚህ የአሳፍ ልጆች በንጉሡ ትእዛዝ ትንቢት ከተናገረው ከአሳፍ እጅ በታች ነበሩ።
25:3b.1CH.025.003ከኤዶታም የኤዶታም ልጆች፤ ጎዶልያስ፥ ጽሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸብያ፥ መቲትያ፥ እነዚህ ስድስቱ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ክብር በመሰንቆ ትንቢት ከተናገረው ከአባታቸው ከኤዶታም እጅ በታች ነበሩ።
25:4b.1CH.025.004ከኤማን የኤማን ልጆች፤ ቡቅያ፥ መታንያ፥ ዓዛርዔል፥ ሱባኤ፥ ኢያሪሙት፥ ሐናንያ፥ ሐናኒ፥ ኤልያታ፥ ጊዶልቲ፥ ሮማንቲዔዘር፥ ዮሽብቃሻ፥ መሎቲ፥ ሆቲር፥ መሐዝዮት፤
25:5b.1CH.025.005እነዚህ ሁሉ ቀንደ መለከቱን ከፍ ያደርጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ቃል የንጉሡ ባለ ራእይ የሆነው የኤማን ልጆች ነበሩ። እግዚአብሔርም ለኤማን አሥራ አራት ወንዶች ልጆችንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ሰጠው።
25:6b.1CH.025.006እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና በመሰንቆም ይዘምሩ ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቤት ያገለግሉ ዘንድ ከአባታቸው እጅ በታች ነበሩ፤ አሳፍም ኤዶታምም ኤማንም ከንጉሡ ትእዛዝ በታች ነበሩ።
25:7b.1CH.025.007የብልሃተኞቹም ቍጥር እግዚአብሔርን ለማመስገን ከሚያውቁ ከወንድሞቻቸው ጋር ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ነበረ።
25:8b.1CH.025.008ሁሉም ተካክለው፥ ታናሹ እንደ ታላቁ፥ አስተማሪውም እንደ ተማሪው፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ።
25:9b.1CH.025.009የፊተኛው ዕጣ ከአሳፍ ወገን ለነበረው ለዮሴፍ ወጣ፤ ሁለተኛው ለጎዶልያስ ወጣ፤ እርሱ ወንድሞቹም ልጆቹም አሥራ ሁለት ነበሩ፤
25:10b.1CH.025.010ሦስተኛው ለዘኩር ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:11b.1CH.025.011አራተኛው ለይጽሪ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:12b.1CH.025.012አምስተኛው ለነታንያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:13b.1CH.025.013ስድስተኛው ለቡቅያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:14b.1CH.025.014ሰባተኛው ለይሽርኤል ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:15b.1CH.025.015ስምንተኛው ለየሻያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:16b.1CH.025.016ዘጠኝኛው ለመታንያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:17b.1CH.025.017አሥረኛው ለሰሜኢ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:18b.1CH.025.018አሥራ አንደኛው ለዓዛርኤል ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:19b.1CH.025.019አሥራ ሁለተኛው ለሐሸብያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:20b.1CH.025.020አሥራ ሦስተኛው ለሱባኤል ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:21b.1CH.025.021አሥራ አራተኛው ለመቲትያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:22b.1CH.025.022አሥራ አምስተኛው ለኢያሪሙት ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:23b.1CH.025.023አሥራ ስድስተኛው ለሐናንያ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:24b.1CH.025.024አሥራ ሰባተኛው ለዮሽብቃሻ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:25b.1CH.025.025አሥራ ስምንተኛው ለሐናኒ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:26b.1CH.025.026አሥራ ዘጠኝኛው ለመሎቲ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:27b.1CH.025.027ሀያኛው ለኤልያታ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:28b.1CH.025.028ሀያ አንደኛው ለሆቲር ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:29b.1CH.025.029ሀያ ሁለተኛው ለጊዶልቲ ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:30b.1CH.025.030ሀያ ሦስተኛው ለመሐዚዮት ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ፤
25:31b.1CH.025.031ሀያ አራተኛው ለሮማንቲዔዘር ለልጆቹም ለወንድሞቹም ለአሥራ ሁለቱ ወጣ።
26
26:1b.1CH.026.001በረኞችም እንደዚህ ተመደቡ፤ ከቆሬያውያን ከአሳፍ ልጆች የቆሬ ልጅ ሜሱላም።
26:2b.1CH.026.002ሜሱላም ልጆች ነበሩት፤ በኵሩ ዘካርያስ፥ ሁለተኛው ይዲኤል፥ ሦስተኛው ዮዛባት፥
26:3b.1CH.026.003አራተኛው የትኒኤል፥ አምስተኛው ኤላም፥ ስድስተኛው ይሆሐናን፥ ሰባተኛው ኤሊሆዔናይ።
26:4b.1CH.026.004እግዚአብሔርም ባርኮታልና ዖቤድኤዶም ልጆች ነበሩት፤ በኵሩ ሸማያ፥ ሁለተኛው ዮዛባት፥ ሦስተኛው ኢዮአስ፥ አራተኛው ሣካር፥ አምስተኛው ናትናኤል፥
26:5b.1CH.026.005ስድስተኛው ዓሚኤል፥ ሰባተኛው ይሳኮር፥ ስምንተኛው ፒላቲ።
26:6b.1CH.026.006ለልጁም ለሸማያ ደግሞ ልጆች ተወለዱለት፤ ጽኑዓንም ኃያላን ነበሩና በአባታቸው ቤት ሠለጠኑ።
26:7b.1CH.026.007ለሸማያ ልጆች ዖትኒ፥ ራፋኤል፥ ዖቤድ፥ ወንድሞቹም ኃያላን የነበሩ ኤልዛባድ፥ ኤልሁ፥ ሰማክያ።
26:8b.1CH.026.008እነዚህ ሁሉ የዖቤድኤዶም ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም ልጆቻቸውም ወንድሞቻቸውም ለማገልገል ኃያላን የነበሩ የዖቤድኤዶም ልጆች ስድሳ ሁለት ነበሩ።
26:9b.1CH.026.009ለሜሱላም ኃያላን የነበሩ አሥራ ስምንት ልጆችና ወንድሞች ነበሩት።
26:10b.1CH.026.010ከሜራሪም ልጆች ለነበረው ለሖሳ ልጆች ነበሩት፤ አለቃውም ሽምሪ ነበረ፤ በኵር አልነበረም፥ አባቱ ግን አለቃ አደረገው፤
26:11b.1CH.026.011ሁለተኛውም ኬልቅያስ፥ ሦስተኛው ጥበልያ፥ አራተኛው ዘካርያስ ነበረ፤ የሖሳ ልጆችና ወንድሞች ሁሉ አሥራ ሦስት ነበሩ።
26:12b.1CH.026.012እንደ ወንድሞቻቸው ሆነው በእግዚአብሔር ቤት ያገለግሉ ዘንድ የበረኞች የአለቆች ሰሞነኞች እነዚህ ነበሩ።
26:13b.1CH.026.013በበሩም ሁሉ ያገለግሉ ዘንድ በየአባቶቻቸው ቤቶች ታናሹና ታላቁ ተካክለው ዕጣ ተጣጣሉ።
26:14b.1CH.026.014በምሥራቅም በኩል ዕጣ ለሰሌምያ ወደቀ። ለልጁም ብልህ መካር ለሆነው ለዘካርያስ ዕጣ ጣሉ፤ ዕጣውም በሰሜን በኩል ወጣ።
26:15b.1CH.026.015ለዖቤድኤዶም በደቡብ በኩል፥ ለልጆቹም ለዕቃ ቤቱ ዕጣ ወጣ።
26:16b.1CH.026.016ለሰፊንና ለሖሳ በምዕራብ በኩል፥ በዐቀበቱም መንገድ ባለው በሸሌኬት በር በኩል ጥበቃ ከጥበቃ ላይ ዕጣ ወጣ።
26:17b.1CH.026.017በምሥራቅ በኩል ስድስት ሌዋውያን ነበሩ፤ በሰሜን በኩል ለየዕለቱ አራት፥ በደቡብ በኩል ለየዕለቱ አራት፥ ለዕቃ ቤቱም ሁለት ሁለት ነበሩ።
26:18b.1CH.026.018በምዕራብ በኩል በፈርባር መንገድ ላይ አራት፥ በፈርባርም አጠገብ ሁለት ነበሩ።
26:19b.1CH.026.019ከቆሬና ከሜራሪ ልጆች የነበሩ የበረኞች ሰሞን ይህ ነበረ።
26:20b.1CH.026.020ከሌዋውያን አኪያ በእግዚአብሔር ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብትና በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ላይ ተሾሞ ነበር።
26:21b.1CH.026.021የለአዳን ልጆች፤ ለለአዳን የሆኑ የጌድሶናውያን ልጆች፥ ለጌድሶናዊ ለለአዳን የሆኑ የአባቶች ቤቶች አለቆች ይሒኤሊ፤
26:22b.1CH.026.022የይሒኤሊ ልጆች፤ በእግዚአሔር ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብት ላይ የነበሩ ዜቶም፥ ወንድሙም ኢዩኤል።
26:23b.1CH.026.023ከእንበረማውያን፥ ከይስዓራውያን፥ ከኬብሮናውያን፥ ከዑዝኤላውያን፤
26:24b.1CH.026.024የሙሴ ልጅ የጌርሳም ልጅ ሱባኤል በቤተ መዛግብት ላይ ተሾሞ ነበር።
26:25b.1CH.026.025ወንድሞቹም፤ ከአልዓዛር ልጁ ረዓብያ፥ ልጁም የሻያ፥ ልጁም ኢዮራም፥ ልጁም ዝክሪ፥ ልጁም ሰሎሚት መጡ።
26:26b.1CH.026.026ይህ ሰሎሚትና ወንድሞቹ ንጉሡ ዳዊትና የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች የሠራዊቱም አለቆች፥ በቀደሱት በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ሁሉ ላይ ተሾመው ነበር።
26:27b.1CH.026.027በሰልፍም ከተገኘው ምርኮ የእግዚአብሔርን ቤት ለማበጀት ቀደሱ።
26:28b.1CH.026.028ባለ ራእዩም ሳሙኤል፥ የቂስም ልጅ ሳኦል፥ የኔርም ልጅ አበኔር፥ የጽሩያም ልጅ ኢዮአብ የቀደሱት ንዋየ ቅድሳት ሁሉ ከሰሎሚትና ከወንድሞቹ እጅ በታች ነበረ።
26:29b.1CH.026.029ከይስዓራውያን ከናንያና ልጆቹ ሹማምትና ፈራጆች ይሆኑ ዘንድ በውጭው ሥራ በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር።
26:30b.1CH.026.030ከኬብሮናውያን ሐሸብያና ወንድሞቹ፥ ጽኑዓን የነበሩት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፥ ለእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ ለንጉሡም አገልግሎት በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል ባለው በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር።
26:31b.1CH.026.031ከኬብሮናውያንም እንደ አባቶች ቤቶች ትውልዶች የኬብሮናውያን አለቃ ይርያ ነበረ። ዳዊት በነገሠ በአርባኛው ዓመት ይፈልጉአቸው ነበር፤ በእነርሱም መካከል በገለዓድ ኢያዜር ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ተገኙ፤
26:32b.1CH.026.032ወንድሞቹም ጽኑዓን የነበሩት የአባቶች ቤቶች አለቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉሡም ዳዊት ለእግዚአብሔር ጉዳይ ሁሉና ለንጉሡ ጉዳይ በሮቤላውያንና በጋዳውያን በምናሴም ነገድ እኵሌታ ላይ ሹሞች አደረጋቸው።
27
27:1b.1CH.027.001የእስራኤልም ልጆች የአባቶች ቤቶች አለቆችና የሺህ አለቆች የመቶ አለቆችም በክፍሎች ነገር ሁሉ ንጉሡን ያገለገሉትም ሹማምት እንደ ቍጥራቸው እነዚህ ነበሩ። እነዚህም ክፍሎች እያንዳንዳቸው ሀያ አራት ሺህ ሆነው በዓመት ወራት ሁሉ በየወሩ ይገቡና ይወጡ ነበር።
27:2b.1CH.027.002ለመጀመሪያው ወር በአንደኛው ክፍል ላይ የዘብድኤል ልጅ ያሾብዓም ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሀያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
27:3b.1CH.027.003እርሱ ከፋሬስ ልጆች ነበረ፤ ለመጀመሪያው ወር በጭፍራ አለቆች ሁሉ ላይ ተሾሞ ነበር።
27:4b.1CH.027.004በሁለተኛውም ወር ክፍል ላይ አሆሃዊው ዱዲ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሀያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
27:5b.1CH.027.005ለሦስተኛው ወር ሦስተኛው የጭፍራ አለቃ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሀያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
27:6b.1CH.027.006ይህ በናያስ በሠላሳው መካከል ኃያል ሆኖ በሠላሳው ላይ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ልጁ ዓሚዛባድ ነበረ።
27:7b.1CH.027.007ለአራተኛው ወር አራተኛው አለቃ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ ከእርሱም በኋላ ልጁ ዝባድያ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሀያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበር።
27:8b.1CH.027.008ለአምስተኛው ወር አምስተኛው አለቃ ይዝራዊው ሸምሁት ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሀያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
27:9b.1CH.027.009ለስድስተኛው ወር ስድስተኛው አለቃ የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሀያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
27:10b.1CH.027.010ለሰባተኛው ወር ሰባተኛው አለቃ ከኤፍሬም ልጆች የሆነ ፍሎናዊው ሴሌስ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሀያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
27:11b.1CH.027.011ለስምንተኛው ወር ስምንተኛው አለቃ ከዛራውያን የነበረው ኩሳታዊው ሲቦካይ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሀያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
27:12b.1CH.027.012ለዘጠኝኛው ወር ዘጠኝኛው አለቃ ከብንያማውያን የነበረው ዓናቶታዊው አቢዔዜር ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሀያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
27:13b.1CH.027.013ለአሥረኛው ወር አሥረኛው አለቃ ከዛራውያን የነበረው ነጦፋዊው ኖኤሬ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሀያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
27:14b.1CH.027.014ለአሥራ አንደኛው ወር አሥራ አንደኛው አለቃ ከኤፍሬም ልጆች የነበረው ጲርዓቶናዊው በናያስ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሀያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
27:15b.1CH.027.015ለአሥራ ሁለተኛው ወር አሥራ ሁለተኛው አለቃ ከጎቶንያል ወገን የነበረው ነጦፋዊው ሔልዳይ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሀያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
27:16b.1CH.027.016በእስራኤልም ነገዶች ላይ እነዚህ ነበሩ በሮቤላውያን ላይ የዝክሪ ልጅ አልዓዛር አለቃ ነበረ፤ በስምዖናውያን የመዓካ ልጅ ሰፋጥያስ፤
27:17b.1CH.027.017በሌዊ ላይ የቀሙኤል ልጅ ሐሸቢያ፤
27:18b.1CH.027.018በአሮን ላይ ሳዶቅ፤ በይሁዳ ላይ ከዳዊት ወንድሞች ኤሊሁ፤ በይሳኮር ላይ የሚካኤል ልጅ ዖምሪ፤
27:19b.1CH.027.019በዛብሎን ላይ የአብድዩ ልጅ ይሽማያ፤ በንፍታሌም ላይ የዓዝሪኤል ልጅ ኢያሪሙት፤
27:20b.1CH.027.020በኤፍሬም ልጆች ላይ የዓዛዝያ ልጅ ሆሴዕ፤ በምናሴ ነገድ እኵሌታ ላይ የፈዳያ ልጅ ኢዩኤል፤
27:21b.1CH.027.021በገለዓድ ባለው በምናሴ ነገድ እኵሌታ ላይ የዘካርያስ ልጅ አዶ፤ በብንያም ላይ የአበኔር ልጅ የዕሢኤል፤
27:22b.1CH.027.022በዳን ላይ የይሮሐም ልጅ ዓዛርኤል፤ እነዚህ የእስራኤል ልጆች ነገዶች አለቆች ነበሩ።
27:23b.1CH.027.023እግዚአብሔር ግን እስራኤልን እንደ ሰማይ ከዋክብት ያበዛ ዘንድ ተናግሮ ነበርና ዳዊት ከሀያ ዓመት በታች የነበሩትን አልቈጠረም።
27:24b.1CH.027.024የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቍጠር ጀመረ፥ ነገር ግን አልፈጸመም፤ ስለዚህም በእስራኤል ላይ ቍጣ ሆነ፥ ቍጥራቸውም በንጉሡ በዳዊት መዝገብ አልተጻፈም።
27:25b.1CH.027.025በንጉሡም ቤተ መዛግብት ላይ የዓዲኤል ልጅ ዓዝሞት ሹም ነበረ፤ በሜዳውም በከተሞችም በመንደሮችም በግንቦችም ቤተ መዛግብት ላይ የዖዝያ ልጅ ዮናታን ሹም ነበረ፤
27:26b.1CH.027.026መሬቱን የሚያበጃጁትና እርሻውን በሚያርሱት ላይ የክሉብ ልጅ ዔዝሪ ሹም ነበረ፤
27:27b.1CH.027.027በወይንም ቦታዎች ላይ ራማታዊው ሰሜኢ ሹም ነበረ፤ ለወይንም ጠጅ ዕቃ ቤት በሚሆነው በወይኑ ሰብል ላይ ሸፋማዊው ዘብዲ ሹም ነበረ፤
27:28b.1CH.027.028በቈላውም ውስጥ ባሉት በወይራውና በሾላው ዛፎች ላይ ጌድራዊው በአልሐናን ሹም ነበረ፤ በዘይቱም ቤቶች ላይ ኢዮአስ ሹም ነበረ፤
27:29b.1CH.027.029በሳሮንም በሚሰማሩ ከብቶች ላይ ሳሮናዊው ሰጥራይ ሹም ነበረ፤ በሸለቆቹም ውስጥ በነበሩት ከብቶች ላይ የዓድላይ ልጅ ሻፍጥ ሹም ነበረ፤
27:30b.1CH.027.030በግመሎችም ላይ እስማኤላዊው ኡቢያስ ሹም ነበረ፤ በአህዮቹም ላይ ሜሮኖታዊው ይሕድያ ሹም ነበረ፤
27:31b.1CH.027.031በመንጎቹም ላይ አጋራዊው ያዚዝ ሹም ነበረ። እነዚህ ሁሉ በንጉሡ በዳዊት ሀብት ላይ ሹሞች ነበሩ።
27:32b.1CH.027.032አስተዋይና ጸሐፊ የነበረው የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል ከንጉሡ ልጆች ጋር ነበረ፤
27:33b.1CH.027.033አኪጦፌልም የንጉሡ አማካሪ ነበረ፤ አርካዊውም ኩሲ የንጉሡ ወዳጅ ነበረ፤
27:34b.1CH.027.034ከአኪጦፌልም ቀጥሎ የበናያስ ልጅ ዮዳሄና አብያታር ነበሩ፤ ኢዮአብም የንጉሡ ሠራዊት አለቃ ነበረ።
28
28:1b.1CH.028.001ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉ፥ የነገዶቹንም አለቆች፥ ንጉሡንም በክፍል የሚያገለግሉትን የጭፍሮች አለቆች፥ ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆችንም፥ በንጉሥና በልጆች ሀብትና ግዛት ላይ የተሾሙትን፥ ጃንደረቦችንም፥ ጽኑዓን ኃይላኑንም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
28:2b.1CH.028.002ንጉሡም ዳዊት በእግሩ ቆሞ እንዲህ አለ። ወንድሞቼና ሕዝቤ ሆይ፥ ስሙኝ፤ ለእግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦትና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የዕረፍት ቤት ለመሥራት እኔ በልቤ አስቤአለሁ፤ ለሥራም የሚያስፈልገውን አዘጋጅቻለሁ፤
28:3b.1CH.028.003እግዚአብሔር ግን። የሰልፍ ሰው ነህና፥ ደምም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም ብሎኛል።
28:4b.1CH.028.004ነገር ግን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ የዘላለም ንጉሥ እሆን ዘንድ ከአባቴ ቤት ሁሉ መርጦኛል፤ ይሁዳም አለቃ ይሆን ዘንድ መርጦታል፤ ከይሁዳም ቤት የአባቴን ቤት መርጦአል፤ ከአባቴም ልጆች መካከል በእስራኤል ሁሉ ላይ ያነግሠኝ ዘንድ ሊመርጠኝ ወደደ።
28:5b.1CH.028.005እግዚአብሔርም ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን መርጦታል።
28:6b.1CH.028.006እርሱም። ልጅ ይሆነኝ ዘንድ መርጬዋለሁና፥ እኔም አባት እሆነዋለሁና ልጅህ ሰሎሞን ቤቴንና አደባባዮቼን ይሠራል።
28:7b.1CH.028.007ትእዛዜንና ፈርዴንም በማድረግ እንደ ዛሬው ቢጸና መንግሥቱን ለዘላለም አጸናዋለሁ አለኝ።
28:8b.1CH.028.008አሁንም የእግዚአብሔር ጉባኤ እስራኤል ሁሉ እያዩ፥ አምላካችንም እየሰማ፥ ይህችን መልካሚቱን ምድር ትወርሱ ዘንድ፥ ለልጆቻችሁም ለዘላለም ታወርሱአት ዘንድ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ፥ ፈልጉም።
28:9b.1CH.028.009አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና፥ የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘላለም ይጥልሃል።
28:10b.1CH.028.010አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለመቅደስ የሚሆን ቤትን ትሠራ ዘንድ መርጦሃልና ጠንክረህ ፈጽመው።
28:11b.1CH.028.011ዳዊትም ለመቅደሱ ወለል፥ ለቤቱም፥ ለቤተ መዛግብቱም፥ ለደርቡና ለውስጡም ጓዳዎች፥ ለስርየቱም መክደኛ መቀመጫ ምሳሌውን ለልጁ ለሰሎሞን ሰጠው።
28:12b.1CH.028.012ደግሞም ለእግዚአብሔር ቤት አደባባዮችና በዙርያው ለሚሆኑ ጓዳዎች፥ ለእግዚአብሔርም ቤት ለሚሆኑ ቤተ መዛግብት፥ ለንዋየ ቅድሳቱም ለሚሆኑ ቤተ መዛግብት በመንፈሱ ላሰበው ሁሉ ምሳሌን ሰጠው።
28:13b.1CH.028.013የካህናቱንና የሌዋውያኑንም ክፍላቸውን በእግዚአብሔርም ቤት በሚያገለግሉበት ሥራ ሁሉ አስታወቀው። በእግዚአብሔርም ቤት ለሚያገለግሉበት ዕቃ ሁሉ፥ ለአገልግሎት ሁሉ ለሚሆነውም ለወርቁ ዕቃ ወርቁን በሚዛን ሰጠው፤ ለአገልግሎት ሁሉ ለሚሆነውም ለብር ዕቃ ሁሉ ብሩን በሚዛን ሰጠው፤
28:15b.1CH.028.015ለወርቁም መቅረዞችና ለቀንዲሎችም ወርቁን በየመቅረዙና በየቀንዲሉ በሚዛን ሰጠው፤ ለብሩን መቅረዞች እንደ መቅረዙ ሁሉ ሥራ ሁሉ ብሩን በየመቅረዙና በየቀንዲሉ በሚዛን ሰጠው፤
28:16b.1CH.028.016ለገጹ ኅብስት ገበታዎች ወርቁን በሚዛን ለገበታዎቹ ሁሉ፥ ብሩንም ለብሩ ገበታዎች ሰጠው፤
28:17b.1CH.028.017ለሜንጦቹና ለድስቶቹ ለመቅጃዎቹም ጥሩውን ወርቅ፥ ለወርቁም ጽዋዎች ወርቁን በየጽዋው ሁሉ በሚዛን፥ ለብሩም ጽዋዎች ብሩን በየጽዋው ሁሉ በሚዛን ሰጠው፤
28:18b.1CH.028.018ለዕጣኑም መሠዊዋ ጥሩውን ወርቅ በሚዛን፥ ክንፎቻቸውንም ዘርግተው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት የሸፈኑትን የኪሩቤልን የወርቅ ሰረገላ ምሳሌ ሰጠው።
28:19b.1CH.028.019ዳዊትም። የሥራውን ሁሉ ምሳሌ አውቅ ዘንድ ይህ ሁሉ በእግዚአብሔር እጅ ተጽፎ መጣልኝ አለ።
28:20b.1CH.028.020ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን። ጠንክር፥ አይዞህ፥ አድርገውም፤ አምላኬ እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፥ አትደንግጥም፤ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነው ሥራ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ እርሱ አይተውህም፥ አይጥልህምም።
28:21b.1CH.028.021እነሆም፥ ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ሁሉ የሚሆኑ የካህናትና የሌዋውያን ክፍሎች በዚህ አሉ፤ ለሁሉም ዓይነት አገልግሎትና ሥር በብልሃትና በነፍሱ ፈቃድ የሚሠራ ሁሉ ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አለቆችና ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው ይታዘዙሃል አለው።
29
29:1b.1CH.029.001ንጉሡም ዳዊት ለጉባኤው ሁሉ እንዲህ አለ። እግዚአብሔር ብቻውን የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ብላቴና ለጋ ነው፤ ሕንፃው ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክ ነው እንጂ ለሰው አይደለምና ሥራው ታላቅ ነው።
29:2b.1CH.029.002እኔም እንደ ጕልበቴ ሁሉ ለአምላኬ ቤት ለወርቁ ዕቃ ወርቁን፥ ለብሩም ዕቃ ብሩን፥ ለናሱም ዕቃ ናሱን፥ ለብረቱም ዕቃ ብረቱን፥ ለእንጨቱም ዕቃ እንጨቱን፥ ደግሞም መረግድንና በፈርጥ የሚገባ ድንጋይን፥ የሚለጠፍ ድንጋይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለውንም ድንጋይ፥ የከበረውንም ድንጋይ ከየዓይነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘጋጅቻለሁ።
29:3b.1CH.029.003ከዚህም በላይ ደግሞ የአምላኬን ቤት ስለወደድሁ፥ ለመቅደሱ ካዘጋጀሁት ሁሉ ሌላ የግል ገንዘቤ የሚሆን ወርቅና ብር አለኝና ለአምላኬ ቤት ሰጥቼዋለሁ።
29:4b.1CH.029.004የቤቶቹ ግንብ ይለበጡበት ዘንድ ከኦፊር ወርቅ ሦስት ሺህ መክሊት ወርቅ፥ ሰባት ሺህም መክሊት ጥሩ ብር፥
29:5b.1CH.029.005በሠራተኞች እጅ ለሚሠራው ሥራ ሁሉ ለወርቁ ዕቃ ወርቁን፥ ለብሩም ዕቃ ብሩን ሰጥቻለሁ። ዛሬ በፈቃዱ ራሱን ለእግዚአብሔር የሚቀድስ ማነው?
29:6b.1CH.029.006የአባቶችም ቤቶች አለቆች፥ የእስራኤልም ነገዶች አለቆች፥ ሻለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ በንጉሡም ሥራ ላይ የተሾሙት በፈቃዳቸው አቀረቡ።
29:7b.1CH.029.007ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት አምስት ሺህ መክሊት ወርቅና አሥር ሺህ ዳሪክ፥ አሥር ሺህም መክሊት ብር፥ አሥራ ስምንት ሺህም መክሊት ናስ፥ መቶ ሺህም መክሊት ብረት ሰጡ።
29:8b.1CH.029.008ዕንቍም ያለው ሰው ሁሉ ለእግዚአብሔር ቤት ለሆነው ቤተ መዛግብት በጌድሶናዊው በይሒኤል እጅ ሰጠ።
29:9b.1CH.029.009ሕዝቡም ፈቅደው ሰጥተዋልና፥ በፍጹም ልባቸውም ለእግዚአብሔር በፈቃዳቸው አቅርበዋልና ደስ አላቸው፤ ንጉሡም ዳዊት ደግሞ ታላቅ ደስታ ደስ አለው።
29:10b.1CH.029.010ዳዊትም በጉባኤው ሁሉ ፊት እግዚአብሔርን ባረከ፤ ዳዊትም አለ። አቤቱ፥ የአባታችን የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ተባረክ።
29:11b.1CH.029.011አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኃይል፥ ክብርም፥ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ፥ መንግሥት የአንተ ነው፥ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ።
29:12b.1CH.029.012ባለጠግነትና ክብር ከአንተ ዘንድ ነው፥ አንተም ሁሉን ትገዛለህ፤ ኃይልና ብርታት በእጅህ ነው፤ ታላቅ ለማድረግ፥ ለሁሉም ኃይልን ለመስጠት በእጅህ ነው።
29:13b.1CH.029.013አሁንም እንግዲህ፥ አምላካችን ሆይ፥ እንገዛልሃለን፥ ለክቡር ስምህም ምስጋና እናቀርባለን።
29:14b.1CH.029.014ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና፥ ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል ችለን ልናቀርብልህ እኔ ማን ነኝ? ሕዝቤስ ማን ነው?
29:15b.1CH.029.015አባቶቻችንም ሁሉ እንደነበሩ እኛ በፊትህ ስደተኞችና መጻተኞች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ናት፥ አትጸናም።
29:16b.1CH.029.016አቤቱ አምላካችን ሆይ፥ ለቅዱስ ስምህ ቤት እንሠራ ዘንድ ይህ ያዘጋጀነው ባለጠግነት ሁሉ ከእጅህ የመጣ ነው፥ ሁሉም የአንተ ነው።
29:17b.1CH.029.017አምላኬ ሆይ፥ ልብን እንድትመረምር፥ ቅንነትንም እንድትወድድ አውቃለሁ፤ እኔም በልቤ ቅንነትና በፈቃዴ ይህን ሁሉ አቅርቤአለሁ፤ አሁንም በዚህ ያለው ሕዝብህ በፈቃዱ እንዳቀረበልህ በደስታ አይቻለሁ።
29:18b.1CH.029.018አቤቱ፥ የአባቶቻችን የአብርሃምና የይስሐቅ የእስራኤልም አምላክ ሆይ፥ ይህን አሳብ በሕዝብህ ልብ ለዘላለም ጠብቅ፥ ልባቸውንም ወደ አንተ አቅና።
29:19b.1CH.029.019ትእዛዝህንም ምስክርህንም ሥርዓትህንም ይጠብቅ ዘንድ፥ ይህንም ነገር ሁሉ ያደርግ ዘንድ፥ ያዘጋጀሁለትንም ቤት ይሠራ ዘንድ ለልጄ ለሰሎሞን ፍጹም ልብ ስጠው።
29:20b.1CH.029.020ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ። አምላካችሁን እግዚአብሔርን ባርኩ አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው ለእግዚአብሔርና ለንጉሡ ሰገዱ።
29:21b.1CH.029.021በነጋውም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሠዉ፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረቡ፤ አንድ ሺህ ወይፈን፥ አንድ ሺህም አውራ በጎች፥ አንድ ሺህም የበግ ጠቦቶች፥ የመጠጥ ቍርባናቸውንም፥ ስለ እስራኤልም ሁሉ ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ።
29:22b.1CH.029.022በዚያም ቀን በታላቅ ደስታ በእግዚአብሔር ፊት በሉ ጠጡም። የዳዊትንም ልጅ ሰሎሞንን ሁለተኛ ጊዜ አነገሡት፤ እርሱንም አለቃ ይሆን ዘንድ ለእግዚአብሔር ቀቡት፥ ሳዶቅንም ካህን ይሆን ዘንድ ቀቡት።
29:23b.1CH.029.023ሰሎሞንም በአባቱ በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀመጠ፥ ተከናወነለትም፤ እስራኤልም ሁሉ ታዘዙለት።
29:24b.1CH.029.024አለቆቹም ሁሉ፥ ኃያላኑም፥ ደግሞም የንጉሡ የዳዊት ልጆች ሁሉ ለንጉሡ ለሰሎሞን እጅ ሰጡት።
29:25b.1CH.029.025እግዚአብሔርም ሰሎሞንን በእስራኤል ሁሉ ፊት እጅግ አገነነው፤ ከእርሱ በፊትም ለነበሩት ለእስራኤል ነገሥታት ያልሆነውን የመንግሥት ክብር ሰጠው።
29:26b.1CH.029.026የእሴይም ልጅ ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ።
29:27b.1CH.029.027በእስራኤልም ላይ የነገሠበት ዘመን አርባ ዓመት ነበረ፤ ሰባት ዓመት በኬብሮን ነገሠ፥ ሠላሳ ሦስትም ዓመት በኢየሩሳሌም ነገሠ።
29:28b.1CH.029.028ዕድሜም፥ ባለጠግነትም፥ ክብርም ጠግቦ በመልካም ሽምግልና ሞተ፤ ልጁም ሰሎሞን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
29:29b.1CH.029.029የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባለ ራእዩ በሳሙኤል ታሪክ፥ በነቢዩም በናታን ታሪክ፥ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፎአል።
29:30b.1CH.029.030እንደዚሁም የመንግሥቱ ነገርና ኃይሉ ሁሉ በእርሱም በእስራኤልም በአገሮችም መንግሥታት ሁሉ ላይ ያለፉት ዘመናት ተጽፈዋል።
- Holder of rights
- Multilingual Bible Corpus
- Citation Suggestion for this Object
- TextGrid Repository (2025). Amharic Collection. 1 Chronicles (Amharic). 1 Chronicles (Amharic). Multilingual Parallel Bible Corpus. Multilingual Bible Corpus. https://hdl.handle.net/21.11113/0000-0016-8A37-F